የሰይጣንን ፡ መኖሪያ ፡ ስናስብ ፡ ያስፈራራል (Yeseyttanin Menoriya Sinasib Yasferaral)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የሰይጣንን ፡ መኖሪያ
ስናስብ ፡ ያስፈራራል
የኩኑናን ፡ መሣቀያ
ልባችንን ፡ ያፈርሳል
ወደ ፡ ሲዖል ፡ እንዳንጠልቅ
እንቅልፍ ፡ እንዳያጠቃን
የፀጋ ፡ ዘመንህ ፡ ሳያልቅ
ኦ! አምላክ ፡ አነቃቃን

ዛፍ ፡ ከተጣለ ፡ ከመሬት
ተመልሶ ፡ አይነሣም
እንዲሁም ፡ ወደ ፡ ሰይጣን ፡ ቤት
የጠለቀ ፡ አይወጣም
ሰው ፡ በሲዖል ፡ ስሕተቱን
ቢያምን ፡ ምን ፡ ይረባል?
በዚያ ፡ ኃጥዕ ፡ ብድሩን
እንደ ፡ ሥራው ፡ ያገኛል

ከሞት ፡ በኋላ ፡ ንስሐ
መግባት ፡ ከቶ ፡ አይቻልም
አምላክ ፡ ይሰጣል ፡ ፍስሐ
ለፈራው ፡ በዚህ ፡ ዓለም
ኃጢአን ፡ ግን ፡ ከአምላክ ፡ ፊት ፡ ርቀው
ሥቃይ ፡ ይቀበላሉ
ዘለዓለምም ፡ ተጨንቀው
ከሰይጣን ፡ ጋራ ፡ አሉ

ሰው ፡ ሆይ! ፍራ! ተቀጥቀጥም
ሲዖል ፡ ተከፈተብህ
ለመንገድህ ፡ ተጠንቀቅም
ገሃነም ፡ እንዳይውጥህ
ከዲን ፡ እሣት ፡ እንድትድን
በኢየሱስ ፡ የሚያምን
ልብ ፡ እንዲሰጥህ ፡ አምላክን
በምሉዕ ፡ ነፍስህ ፡ ለምን

ኦ! አምላካችን ፡ አድነን
በቁጣህ ፡ አትጣለን
የትልቅ ፡ በደላችንን
ቅጣት ፡ አታውርድብን
በዕውነተኛ ፡ ሃይማኖት
ልባችንን ፡ አንጻልን
በዕምነት ፡ ጸንተን ፡ ብንሞት
ከሞት ፡ እንድናለን