የአብ ፡ ሥምረት ፡ ተገለጠች (YeAb Simret Tegeletech)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የዓብ ፡ ሥምረት ፡ ተገለጠች
ንጽሕት ፡ ድንግል ፡ ወለደች
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ተወልዷል
በዕጹብ ፡ ያስደንቃል

ግሩም ፡ ተአምራት ፡ አይተናል
በአምላክ ፡ መንፈስ ፡ ሆኗል
የዘለዓለም ፡ የአምላክ ፡ ቃል
እንደ ፡ ሰው ፡ ተወልዷል

ሳይደርስበት ፡ ኃጢአት
የሰውን ፡ ሁሉ ፡ ኃጢአት
የሚሽር ፡ ተወለደ
ከሥጋም ፡ ተዋሐደ

ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ፍፁም ፡ ሰው
በመሆኑ ፡ መድኅን ፡ ነው
በሥቃይና ፡ ሕማም
አግኝቶልናል ፡ ሰላም

ጥንት ፡ ከዓብም ፡ ወጥቷል
ወደ ፡ ዓብም ፡ ዓርጓል
በቀኙም ፡ ተቀምጧል
ሁሉም ፡ ይገዛለታል!

ሞትን ፡ በአምላካዊ ፡ ኃይል
ለዘለዓለም ፡ ሽሯል
ድል ፡ በብርቱ ፡ ውጊያ
ነሥቷል ፡ ሃሌ ፡ ሉያ!

አምላክን ፡ በዓርያም
እናመስግን ፡ በሰላም!
እኛን ፡ መንፈሱም ፡ ይምራን
ምድሪቱም ፡ ጽድቅ ፡ ታፍራ