ወዳምላክ ፡ ልብ ፡ የሚያደርስ (WodeAmlak Lib Yemiyaders)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወዳምላክ ፡ ልብ ፡ የሚያደርስ
አንድ ፡ ቅዱስ ፡ ደጅ ፡ አውቃለሁ
ከዚያም ፡ ደጅ ፡ ብርሃን ፡ ሲሠርጽ
መድኃኒቴን ፡ አያለሁ
እንዴት ፡ ይገርማል ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለኔ
ለእኔ ፣ ለእኔ
ተከፈተ ፡ ለእኔ

ያ ፡ ደጅ ፡ ለማንም ፡ አይዘጋም
ተከፈተ ፡ ለሁሉ
ለንጉሥም ፡ ለባሪያም
ለምድር ፡ ወገን ፡ ሁሉ
እንዴት ፡ ይገርማል ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለኔ
ለእኔ ፣ ለእኔ
ተከፈተ ፡ ለእኔ

አንድ ፡ ቀን ፡ ግን ፡ ደጁ ፡ ይዘጋል
ቶሎ ፡ ለመግባት ፡ ቸኩል
ኢየሱስ ፡ አሁን ፡ ይጠራሃል
ሥጦታውንም ፡ ተቀበል
እንዴት ፡ ይገርማል ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለኔ
ለእኔ ፣ ለእኔ
ተከፈተ ፡ ለእኔ

አንድ ፡ ቀንም ፡ መስቀላችንን
በላይ ፡ ሲያጠፋልን
ዘውድም ፡ ሲሰጠን ፡ ኢየሱስን
እናመሰግናለን
እንዴት ፡ ይገርማል ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለኔ
ለእኔ ፣ ለእኔ
ተከፈተ ፡ ለእኔ