ኦ ፡ ግሩም ፡ ጠቅላይ ፡ ጌታ (O Grum Teqlai Geta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ ግሩም ፡ ጠቅላይ ፡ ጌታ
ሁሉን ፡ የሚገዛ
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
አትፍረድብን
ምሕረት ፡ አድርግልን
ቅዱስ ፡ መንገድህን ፡ አሳየን
ሁሉ ፡ ቀን ፡ አምላክን
ከመላዕክቱ ፡ ማኅበር
በደስታ ፡ እናክብር

ለፈጣሪ ፡ ክብረት
ዕልል ፡ በል ፡ ኦ ፡ ፍጥረት
በልዩ ፡ ድምጽ ፡ ዘምርለት
በእሣት ፡ የጋልሽ
ብርሃን ፡ የመላብሽ
አንቺ ፡ አብሪ ፡ ለፈጣሪሽ
አዕላፎች ፡ ኮከቦች
ጨረቃም ፡ ይዘምሩ
ሥልጣኑን ፡ ያሳዩ

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ለጌታ
አቅርቢ ፡ ምሥጋና
ቤቱን ፡ ገብተሽ ፡ በዕልልታ
ይስገዱለት ፡ ሁሉ
ለክብሩ ፡ ይኑሩ
በቅናት ፡ ግዛቱን ፡ ያስፉ
በዓለም ፡ ላይ ፡ በሰማይ
በዘለዓለም ፡ ዘመን
ይመስገን ፡ ጌታችን