ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው (Eyesusie Lenie Giette Niew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ቅርሴ
(ሌላ ፡ ነገር ፡ አልመኝም
እንደ ፡ እርሱ ፡ አያረካኝም) ፪X

የሕይወትን ፡ ጐዳና ፣ ሜዳና ፡ ተራራ
እስከዛሬ ፡ ስጓዝ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋራ
ለአንበሣና ፡ ለድብ ፡ ሲሰጥ ፡ አላየሁም
እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ ሊያብስ ፡ አይሰለችም ።

አዝ ፣
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ቅርሴ
(ሌላ ፡ ነገር ፡ አልመኝም
እንደ ፡ እርሱ ፡ አያረካኝም) ፪X

ሰው ፡ በሃብቱ ፡ ይመካል ፡ በሚኖረው ፡ ንብረት
በዚች ፡ ከንቱ ፡ ምድር ፡ ባከማቸው ፡ ጥሪት
ሌላ ፡ ምንም ፡ የለኝ ፡ ብር ፡ ወርቄ ፡ የምለው
እኔን ፡ ግን ፡ ያረካኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ።

አዝ ፣
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ቅርሴ
(ሌላ ፡ ነገር ፡ አልመኝም
እንደ ፡ እርሱ ፡ አያረካኝም) ፪X

ለእኔ ፡ ሥም ፡ የለኝም ፡ ስሜ ፡ የኢየሱስ ፡ ነው
ወላጄ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ በሥም ፡ የምጠራው
ለእኔ ፡ ትዳር ፡ የለኝ ፡ ትዳሬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሌት ፡ ተቀን ፡ ስለእኔ ፡ ዘወትር ፡ የሚያስበው

አዝ ፣
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ቅርሴ
(ሌላ ፡ ነገር ፡ አልመኝም
እንደ ፡ እርሱ ፡ አያረካኝም) ፪X

ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ የሚወደኝ ፡ የምወደው
በእኔና ፡ በእርሱ ፡ መሃል ፡ ማነው ፡ የሚገባው?
ሰው ፡ ያለውን ፡ ይበል ፡ እኔስ ፡ አወራለሁ
በማንም ፡ በምንም ፡ የማልለውጠው ፡ ነው ።

አዝ ፣
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ለእኔ ፡ ጌጤ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ቅርሴ
(ሌላ ፡ ነገር ፡ አልመኝም
እንደ ፡ እርሱ ፡ አያረካኝም) ፪X