From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ በክብር ፡ ልናየው
ተዳርሷል ፡ ጊዜያቱ ፡ ልንቀበለው (፪x)
በግርማ ፡ ሲገለጥ ፡ በአሕዛብ ፡ ለመፍረድ
ምንኛ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ ፡ ለክብሩ ፡ የቆምኩት?
አዝ፦ በክብር ፡ ልናየው
ተዳርሷል ፡ ጊዜያቱ ፡ ልንቀበለው (፪x)
ለነፍሣችን ፡ ዕረፍት ፡ ሊሰጥ ፡ ጌታችን
ቀናቱ ፡ ተዳርሷል ፡ ሊሰበስበን
አዝ፦ በክብር ፡ ልናየው
ተዳርሷል ፡ ጊዜያቱ ፡ ልንቀበለው (፪x)
ተንቀው ፡ የነበሩት ፡ ፃድቃን ፡ ደስ ፡ ሲላቸው
የዓለም ፡ ልጆች ፡ ግን ፡ ለቅሶ ፡ ነው ፡ ግብዣቸው
አዝ፦ በክብር ፡ ልናየው
ተዳርሷል ፡ ጊዜያቱ ፡ ልንቀበለው (፪x)
ተስፋ ፡ ሳንቆርጥ ፡ በክፉ ፡ ምኞት
በዕምነት ፡ እንቁም ፡ ጌታችንን ፡ ለማየት
አዝ፦ በክብር ፡ ልናየው
ተዳርሷል ፡ ጊዜያቱ ፡ ልንቀበለው (፪x)
|