በዕውነት ፡ በአንተ ፡ ያመነው (BeEwunet Bante Yamenew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በዕውነት ፡ በአንተ ፡ ያመነው
ኦ! ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ብፁዕ ፡ ነው
ቤዛችን ፡ አንተ ፡ ሁነሃል
በአንተም ፡ ዓብ ፡ ይወደናል

የነፍሴ ፡ ቤዛ ፡ ለመሆን
በሞት ፡ ሕማም ፡ ያደረግኸውን
ያን ፡ ሁሉ ፡ ለእኔ ፡ አድርገሃል
በአምላኬም ፡ ፊት ፡ ያጸድቀኛል

ከፀጋ ፡ ሁሉ ፡ የሚበልጥ
ከአምላክ ፡ መቅሠፍት ፡ እንዳመልጥ
ዕዳዬን ፡ እንደከፈልኸው
በፍቅርህ ፡ ስታስረዳኝ ፡ ነው

በሞትህ ፡ ኦ! መድኃኒቴ
ሕግንም ፡ ፈጸምኸው ፡ ለእኔ
በአንተም ፣ ኦ! ኢየሱስ ፡ ካመንሁ
ምላትህን ፡ ተካፈልሁ

ልጅነት ፡ በአንተ ፡ አግኝቼ
በድፍረት ፡ ወደ ፡ አባቴ
ልቅረብ ፡ ከምድርም ፡ ስለይ
ርስቴን ፡ ልውረሰው ፡ በሰማይ

ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ! ደካማ ፡ ነኝ
በፀጋህ ፡ ኃይል ፡ አጠንክረኝ
ሰይጣን ፡ እንዳያሸንፈኝ
ዘወትር ፡ አንተ ፡ ጠብቀኝ

የጀመርህልኝን ፡ ሥራ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ሥራ
ወትሮም ፡ በመንገድህ ፡ ምራኝ
ወደ ፡ ሰማይህም ፡ ጥራኝ