በአንተ (Bante) - ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ
(Yishak Sedik)

Lyrics.jpg


(2)

ይወደናል
(Yiwedenal)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Yishak Sedik)

እኔ ግን ኣምላኬ ባንተ ደስ ይለኛል
ሃሴት ሆነኸኛል
ምሕረትህን ታምኖ ልቤን ኣርፎብሃል
             ሰላሜ ሆነሃል
            ውስጤ አርፎብሃል
             ደስታዬ ሆነሃል
             ልቤ ጸንቶብሃል

በለስ እንኳን ባታፈራ
ቢጎድል የወይራ ስራ
እርሾችም መብልን ባይሰጡ
ምንም ባይገኝ በጋጡ
         እኔ ግን እየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል
         ሃሴት አደርጋለሁ ሃይል ሆነኸኛል

አምላኬ ሆይ ወዳንተ መቅረብ ይሻለኛል
ያላንተ ዓለም ትርፉ ሃጥኡ ምኑ ያስቀናል
ወደመቅደስ ገብቼ ክብርህን አግኝቶኛል
በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ደስታህ ይበቃኛል

እኔ ግን አምላኬ ባንተ ደስ ይለኛል
ሃሴት ሆነኸኛል
ምሕረትህን ታምኖ ልቤን ኣርፎብሃል
             ሰላሜ ሆነሃል
            ውስጤ አርፎብሃል
             ደስታዬ ሆነሃል
             ልቤ ጸንቶብሃል

በለስ እንኳን ባታፈራ
ቢጎድል የወይራ ስራ
እርሾችም መብል ባይሰጡ
ምንም ባይገኝ በጋጡ
         እኔ ግን እየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል
         ሃሴት አደርጋለው ሃይል ሆነህልኛል

አንተ የሌለህበት ጥጋብ ተድላና ፍስሃ
ተጠምቶ እንደ መቃጠል ነው በደረቅ በርኻ
ልዩነቴ እኮ ነህ ጌታ ዓለመኞች ያጡህ
የምታረካ የህይወት ውሃ ነህ ለጠጡህ

ሰላሜ ሆነሃል
ውስጤ አርፎብሃል
ደስታዬ ሆነሃል
ልቤ ጸንቶብሃል