ምሥጋና ፡ ይገባሃል (Mesgana Yegebahal) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ
ከቶ ፡ ማን ፡ ተገኝቷል ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክብርም ፡ ይገባሃል
መወደስ ፡ ይገባሃል ፡ መንገሥም ፡ ይገባሃል

የመጀመሪያውና ፡ የመጨረሻው
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለው ፡ የሚመጣው
የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የታረድከው
በደምህ ፡ እድፈቴን ፡ ያጠብከው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ
ከቶ ፡ ማን ፡ ተገኝቷል ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክብርም ፡ ይገባሃል
መወደስ ፡ ይገባሃል ፡ መንገሥም ፡ ይገባሃል

እስራታችንን ፡ የበጣጠስከው
ቀንበራችንን ፡ ደግሞ ፡ የሰበርከው
አርነታችንን ፡ በደምህ ፡ ያወጅከው
በላይ ፡ በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ ያለኸው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ
ከቶ ፡ ማን ፡ ተገኝቷል ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክብርም ፡ ይገባሃል
መወደስ ፡ ይገባሃል ፡ መንገሥም ፡ ይገባሃል

ዋጋችንን ፡ ልትሰጠን ፡ ልታሳርፈን
በማይነገር ፡ ሀሴት ፡ ልታስደስተን
በጽዬን ፡ ውስጥ ፡ እፎይ ፡ ልታሰኘን
የምትመጣው ፡ እኛን ፡ ልታጽናናን

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ
ከቶ ፡ ማን ፡ ተገኝቷል ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክብርም ፡ ይገባሃል
መወደስ ፡ ይገባሃል ፡ መንገሥም ፡ ይገባሃል


Navigation menu