መልክህን ፡ ጌታዬ (Melkehen Gietayie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መልክህን ፡ ጌታዬ ፡ ጸሃይ ፡ አክስሎታል
በሃሩሩ ፡ ብዛት ፡ ከስተህ ፡ ገርጥተሃል
ምቾትም ፡ ድሎትም ፡ አልነበረህም ፡ ጌታ
ለሰበዓዊው ፡ ፍጥረት ፡ በስቃይ ፡ ተመታ (፪x)

የሞት ፡ ፅዋ ፡ ቀርባ ፡ ፈዋሼ ፡ ሲጨነቅ
የአባቱ ፡ ድምፅ ፡ ርቆት ፡ በጭንቀት ፡ ሲሳቀቅ
አንጀቱ ፡ ተጣብቆ ፡ አጥንቱ ፡ ሰልስሎ
የእኔን ፡ ሕይወት ፡ ዋጀ ፡ ጌታዬ ፡ ተጋድሎ (፪x)

ተራራ ፡ እየቧጠጥክ ፡ በመዳህ ፡ ስትወጣ
ሆንክልኝ ፡ መድህኔ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ከርታታ
ለአንተ ፡ የጣር ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የፈውስ ፡ ዕለት
ራስህን ፡ አጋልጠህ ፡ ፈፀምከው ፡ በትዕግሥት (፪x)


Navigation menu