ኃይልን ፡ ቀምሼ (Haylen Qemeshie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኃይልህን ፡ ቀምሸ ፡ ክንድህን ፡ አይቼ
ክብርህ ፡ ተንሰራፍቶ ፡ በዓይኔ ፡ ተመልክቼ
ያን ፡ ሁሉ ፡ ዘነጋሁ ፡ ዓለምን ፡ አይቼ
ልሄድም ፡ ተመከርኩ ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ

አንተ ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ጠብቀኝ ፡ ልጅህን
እግሬን ፡ ልትመልሰው ፡ ልትረዳኝ ፡ ፍጠን (፪x)

ፍቅርህ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልለይህ
ኮብልዬም ፡ ብጠፋ ፡ ከድሎት ፡ ደጅህ
ከችጋሩ ፡ ሌላ ፡ ፀጋ ፡ ምህረትህ
አያስጨክኑኝም ፡ ትዝታዎችህ

ከቤትህ ፡ ሸሽቼ ፡ ወዴት ፡ እደርሳለሁ
ከመንፈስህ ፡ ርቄ ፡ ወደማን ፡ እሄዳለሁ (፪x)

ምድሪቱ:አንገላታኝ ፡ አላማዬን ፡ ስቼ
ወደ ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ
ኃጥዕ ፡ ሲለመልም ፡ ሲቀናው ፡ አይቼ
ፍጻሜውን ፡ ሳላይ ፡ በሥራው ፡ ቀንቼ

ፍሬ ፡ የሌለው ፡ ከንቱ ፡ ለካስ ፡ ባዶ ፡ ኖሯል
ግን ፡ የእኔው ፡ ደስታ ፡ ከዓለም ፡ ይልቃል (፪x)

ነፍሴ ፡ ተንገድግዳ ፡ ልትወድቅ ፡ ነበረ
ግን ፡ ድጋፍ ፡ አገኘች ፡ ጠላቴም ፡ አፈረ
የምን ፡ መታለል ፡ ነው ፡ ጉዳቴስ ፡ የቱ ፡ ነው
ተደላድያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ በቀኝ ፡ ነው

አረጋግጦልኛል ፡ ጌታ ፡ እንደማይተወኝ
ጠላት ፡ ተስፋ ፡ ቁረጥ ፡ አትችልም ፡ ልትጥለኝ (፪x)


Navigation menu