ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ (Leniem Abatie Hoy) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መዋረዳቸውን ፡ አይተህ ፡ አንተ ፡ ይቅር ፡ በላቸው
የቤትህን ፡ ልጆች ፡ አንተ ፡ ይቅር ፡ በላቸው
ትዕቢታቸው ፡ ቀርቶ ፡ በትህትና ፡ ልባቸው
እንባቸውን ፡ ሲያፈሱስ ፡ ለአንተ ፡ አየኋቸው

አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ
እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ
ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x)

ጌታ ፡ ዘወትር ፡ መሰበርን ፡ ሽቼ
አብዝቼ ፡ እጮሃለሁ ፡ ሌተቀን ፡ ተግቼ
እስከመቸ ፡ ድረስ ፡ ሕይወቴ ፡ እንዲህ ፡ ደርቆ
እኖራለሁ ፡ ጌታ ፡ ልምላሜ ፡ አርጐ

አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ
እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ
ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x)

የመሰበር ፡ ፍላጐቴ ፡ ግለቱ ፡ ሳይበርድ
ሰማዬችን ፡ ከፍተህ ፡ ምነው ፡ ብትወርድ
ምርኩዜን ፡ ፈትነህ ፡ እባክህ ፡ ስበረኝ
ትሁትና ፡ ታዛዥ ፡ መሆን ፡ አስተምረኝ

አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ
እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ
ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x)

የራሴን ፡ ማንነት ፡ ያኔ ፡ በርግጥ ፡ እረዳለሁ
የውስጥ ፡ ዓይኔ ፡ በርቶ ፡ አብዝቼም ፡ አያለሁ
በፍፁም ፡ ግልጽነት ፡ ስምህን ፡ አውጃለሁ
በበረከት ፡ ሙላት ፡ አስከብርሃለሁ

አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ
እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ
ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x)


Navigation menu