ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ (Feqadehen Endaderg) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የልቤን ፡ ስፈጽም ፡ አምላኬን ፡ ሳልፈራ
ለኋለኛው ፡ ዘመን ፡ ሳከማች ፡ መከራ
ኃጢአትን ፡ ስዘራ ፡ የኖርኩትን ፡ ኑሮ
ፀጋህ ፡ አሳመረው ፡ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x)

አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ
በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x)

ፈቃድህን ፡ አውቆ ፡ መታዘዙ ፡ ጠቅሞኝ
ከኃጢአትም ፡ መራቅ ፡ ማስተዋል ፡ ሆኖልኝ
መልካም ፡ ሥርዓትህን ፡ ተምሬ ፡ ተምሬ
በእንግድነት ፡ ሐገር ፡ እዘምራለሁ ፡ ዛሬ

አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ
በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x)

ፈቃድህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ የፈጸምከው ፡ በእኔ
ለዛሬም ፡ ለነገም ፡ ባንተ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ዓይኔ
በምሄድበትም ፡ መንገዴን ፡ አሳየኝ
በቀረልኝ ፡ ዘመን ፡ ፈቃድህን ፡ አስታውቀኝ (፪x)

አዝ፦ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳስተውል ፡ አርገኝ
በቀረልኝ ፡ ዘመኔ ፡ ፈቃድህን ፡ እንዳደርግ ፡አስተምረኝ (፪x)


Navigation menu