ምህረቱ (Meheretu) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

አዝአቤት (፫x) ፡ ይሄ ፡ ጌታ
አቤት (፫x) ፡ ምህረቱ (፪x)

አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምህረቱ ፡ እሆሆ (፫x)
አቤት ፡ ቸርነቱ ፡ ቸርነቱ ፡ አሃሃ (፫x)
አቤት ፡ በጐነቱ ፡ በጐነቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)

ምህረት ፡ በዛ ፡ ለምስኪኑ
ተስፋ ፡ አለው ፡ በዘመኑ
ተቆጠረ ፡ ከሰው ፡ ጋራ
እርሱ ፡ ይናገር ፡ እርሱ ፡ ያውራ
ስንቱ ፡ አበሳው ፡ ተራግፎለት
እንደሰው ፡ ዛሬ ፡ አምሮበት
በአደባባይ ፡ ቆሞ ፡ ይሄዳል
ይሄ ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ ይገርማል

አዝአቤት (፫x) ፡ ይሄ ፡ ጌታ
አቤት (፫x) ፡ ምህረቱ

አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምህረቱ ፡ እሆሆ (፫x)
አቤት ፡ ቸርነቱ ፡ ቸርነቱ ፡ አሃሃ (፫x)
አቤት ፡ በጐነቱ ፡ በጐነቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)

የተጣለ ፡ ከሰው ፡ ደጃፍ
መከርን ፡ አየ ፡ በስንቱ ፡ አፍ
እዩት ፡ ዛሬ ፡ ይኸው ፡ ቆመ
ደረቁ ፡ ዛፍ ፡ ለመለመ
ጥላ ፡ ሆነ ፡ ለደከሙ
ጠላቶቹ ፡ ሁሉን ፡ ሰሙ
ድንቅ ፡ ተባለ ፡ በምስኪን ፡ ቤት
ባለ ፡ ፈንታ ፡ ሞላው ፡ ሃሴት

አዝ፦ አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምህረቱ ፡ እሆሆ (፫x)
አቤት ፡ ቸርነቱ ፡ ቸርነቱ ፡ አሃሃ (፫x)
አቤት ፡ በጐነቱ ፡ በጐነቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)

የሚሸከም ፡ በዕድሜ ፡ ዘመን
የሚታደግ ፡ ከሰቀቀን
ጽኑ ፡ አለት ፡ የሚያስመካ
አማኑኤል ፡ አለኝ ፡ ለካ
ከእንግዲህስ ፡ ለምን ፡ ልፍራ
ጌታ ፡ እያለኝ ፡ የሚያኮራ
ምህረቱን ፡ እደገፋለሁ
ይህን ፡ አለት ፡ አምነዋለሁ

አዝአቤት (፫x) ፡ ይሄ ፡ ጌታ
አቤት (፫x) ፡ ምህረቱ

አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምህረቱ ፡ እሆሆ (፫x)
አቤት ፡ ቸርነቱ ፡ ቸርነቱ ፡ አሃሃ (፫x)
አቤት ፡ ማፅናናቱ ፡ ማፅናናቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)
አቤት ፡ በረከቱ ፡ በረከቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)
አቤት ፡ ደግነቱ ፡ ደግነቱ ፡ ኦሆሆ (፫x)