ሰው ፡ ከንቱ (Sew Kentu) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

 
እንገናኝ ፡ ነገ ፡ እንገናኝ ፡ ደህና
ዛሬን ፡ ለማደሩ ፡ መች ፡ አወቀውና
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)
መንገዱን ፡ ሲያረዝም ፡ እቅዱን ፡ ሲያሰፋ
ዘንግቶት ፡ ይሆናል ፡ ታይቶ ፡ እንደሚጠፋ
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)

አዝ:- ሰው ፡ ከንቱ (፮x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ብርቱ (፪x)

ጀግና ፡ ወጥቶ ፡ ሲቀር ፡ ጐበዙ ፡ ሲቀጠፍ
ነገን ፡ እያሰቡ ፡ ከዛሬ ፡ አለማለፍ
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)
ብዪ ፡ ጠጪ ፡ እያለ ፡ ነፍሱን ፡ ሲያዝናና
ሞት ፡ እንደ ፡ ደራሽ ፡ ወንዝ ፡ ድንገት ፡ ይመጣና
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)

አዝ:- ሰው ፡ ከንቱ (፮x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ብርቱ (፪x)

ይህ ፡ ለእኔ ፡ ያ ፡ ለእኔ ፡ እዚም ፡ እዚያም ፡ እኔ
ካለው ፡ ካገደመው ፡ ሲቅበዘበዝ ፡ ዓይኔ
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)
የነገሌ ፡ የዘር ፡ ነኝ ፡ ሃብቴም ፡ እንዳፈር
ማንና ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ አብሮኝ ፡ ሚቀበር
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)

አዝ:- ሰው ፡ ከንቱ (፮x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ብርቱ (፪x)

በውበት ፡ መመካት ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ ፡ ማለት
ህልም ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር ፡ ከአፈር ፡ የገቡ ፡ እለት
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)
አስተዋይ ፡ ከዛሬ ፡ የነገን ፡ ይመርጣል
እግዚአብሔርን ፡ ማወቅ ፡ ከሁሉን ፡ ይበልጣል
ሰው ፡ ከንቱ (፪x)

አዝ:- ሰው ፡ ከንቱ (፮x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ብርቱ (፪x)