በቃ ፡ ዳንኩኝ (Beqa Dankugn) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

አንተን ፡ እየሰጋሁ ፡ እኔን ፡ ያመንኩበት
እየጠረጠርኩህ ፡ በእኔ ፡ እርግጥ ፡ የሆንኩበት
ለካ ፡ የከንቱነት ፡ የሞኝነት ፡ ዘመን ፡ ነው
ዛሬ ፡ ግን ፡ ነቅቼ ፡ እምነቴ ፡ ነህ ፡ እላለሁ
ለካ ፡ የከንቱነት ፡ የሞኝነት ፡ ዘመን ፡ ነው
ዛሬ ፡ ግን ፡ ሲገባኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ/ማኅተሜ ፡ እላለሁ (፪x)

አንተ ፡ እምነቴ ፡ ነህ (፭x)
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ
አንተ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ (፪x)
አንተ ፡ ማህተሜ ፡ ነህ (፪x)
አንተ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ እምነቴ ፡ ነህ

ባለማወቅ ፡ ጠንቅ ፡ በልበ ፡ ደንዳናነት ፡ የጨለምኩ
ይህን ፡ ዓለም ፡ ለሚገዛ ፡ ለክፉ ፡ መንፈሥ ፡ ባሪያ ፡ ነበርኩ
በዘላለም ፡ ቁጣ ፡ ተጥዬ ፡ ከአብ ፡ ሕይወት ፡ የራቅኩኝ
ገና ፡ ከፍጥረቴ ፡ ሙት ፡ ነበርኩኝ

የማመጣው ፡ የዋኖስ ፡ ደም ፡ አይደለም ፡ ያነፃኝ
አብን ፡ እንዳየው ፡ ጸጋህ ፡ ነው ፡ የረዳኝ
የማመጣው ፡ የበግ ፡ ደም ፡ አይደለም ፡ ያነፃኝ
አብን ፡ እንዳምነው ፡ ጸጋህ ፡ ነው ፡ የረዳኝ

በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአቅምህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ጸጋህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም

ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ስራህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ትጋትህ

በደሌን ፡ ተሸክመህ ፡ ለዓለም ፡ እና ፡ ለአብ ፡ አንዴ ፡ ታይተሀል
ፅድቅን ፡ አልብሰህ ፡ ለዘላለም ፡ በቀኙ ፡ አኑረሀል
መልከጼዴቄ ፡ ባንተ ፡ እኔ ፡ ዳንኩኝ
ከአቤል ፡ ደም ፡ ባየለ ፡ በደምህ ፡ ነፃሁኝ

ከከንቱ ፡ እሩጫ ፡ ባንተ ፡ ታቅቤ
ሞት ፡ ላይከጅለኝ ፡ መንደር ፡ ቀይሬ
በምሕረትህ ፡ ብርታት ፡ ከጠላት ፡ ኮበለልኩ
ከድካሜ ፡ ይልቅ ፡ ሃይልህንም ፡ አመንኩ

በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ፀጋህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ
በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም

ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ስራህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ፀጋህ
ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ