Samuel Negussie/BeEgziabhier Alem/Ewedehalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{Lyrics

ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ደስ ፡ የሚለኝ ፡ እኔስ ፡ ሁሌ (፪x) ሳወራው ፡ ነው ፡ ሰው ፡ የመሆን ፡ ምክንያቴን ሳወራው ፡ ነው ፡ የመዳኔን ፡ ምክንያቴን

ስለኔ ፡ በመስቀል ፡ ሞተሃል ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ስለኔ ፡ ደምን ፡ አፍሥሰሃል ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ስለኔ ፡ ያልሆንከው ፡ የቱ ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ምክንያትህ ፡ ለኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚያስብልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ ዘላለሜ ፡ ያማረው ፡ ባንተ ፡ ነው

ተስፋ ፡ ያልነበረውን ፡ ያንን ፡ ሂወቴን የሞት ፡ ድምፅ ፡ ቢሰማ ፡ ጨለማው ፡ ቤቴ በፍቅር ፡ ዘልቀህ ፡ ወደ ፡ ውስጠኛው ፡ ልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገብተህ አበራህልኝ ፡ የህይወቴን ፡ ብርሃን ፡ ተስፋህን ፡ ሰጠህ ሰላምህ ፡ ህይወቴን ፡ አጥለቀለቀው የደስታ ፡ ዘይት ፡ ውስጤን ፡ አራሰው ዝምብዬ ፡ አይደለም ፡ በጥዋት ፡ ማታ ፡ እየሱስ ፡ የምለው ፍቅርህ ፡ ታሪኬን ፡ ህይወት ፡ ዘመኔን ፡ መልካም ፡ አርጎት ፡ ነው

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ የሚመቸኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ ዘላለሜ ፡ ያማረው ፡ ባንተ ፡ ነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚያስብልኝ ፡ ማነው

የምህረት ፡ ልብህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ ሁሌ ፡ የሚፈልገኝ ፡ ማይሰለቸኝ ፡ ነህ ምክንያቱ ፡ ሆነህ ፡ ከዘላለም ፡ ሞት ፡ ጥፋት ፡ መትረፌ እንዲህ ፡ በሰላም ፡ እንዲህ ፡ በደስታ ፡ በህይወት ፡ መኖሬ ወደድከኝ ፡ ወደድከኝ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ ተሰቃየህልኝ ፡ ህመሜን ፡ ታመምክ ያን ፡ ሁሉ ፡ ስቃይ ፡ መራራን ፡ ፅዋ ፡ እንዲያ ፡ የጠጣኸው ዛሬየን ፡ አይተህ ፡ በእረፍት ፡ እንድኖር ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ

ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዛሬዬን ፡ አይተህ ፡ ሁሉን ፡ ታገስከኝ ፡ እየሱስ ፡ ወዳጄ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ እወድሃለሁ ፡ ከሞት ፡ ያዳንከኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ውዴ

(መስከረም ፡ ጌቱ)

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚራራልኝ ፡ ማነው እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ የታገሰኝ ፡ ማነው ሰላሜ ፡ ነህ ፡ ሰላሜ ፡ ነህ ፡ ሰላሜ እረፍቴ ፡ ነህ ፡ እረፍቴ ፡ ነህ በጣም ፡ የምወድህ ፡ በጣም ፡ የምወድህ }}