ምንም ፡ በሌለበት (Menem Belielebet) - ሮማን ፡ ሎሬንሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሮማን ፡ ሎሬንሶ
(Roman Lorenso)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው
(Gieta Becha Tamagn New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሎሬንሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Lorenso)

ምንም ፡ በሌለበት ፡ ጭው ፡ ባለው ፡ በረሃ
አጋር ፡ ከነልጇ ፡ ወደዚያ ፡ ተሰዳ
ተደፍታ ፡ ስታለቅስ ፡ ምርር ፡ ያለ ፡ ለቅሶ
ምንጭ ፡ አፈለቀላት ፡ እግዚአብሔር ፡ ደርሶ [1]

ይደርሳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይደርሳል
ይደርሳል ፡ የተጠማ ፡ ያያል
ምንጭን ፡ ያፈልቅና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

መጠጥ ፡ እነደጠጣች ፡ ስካር ፡ እንደያዛት
ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ እንኳን ፡ ሃናን ፡ ጠረጠራት
እርሷ ፡ ግን ፡ የውስጧን ፡ ችግሯን ፡ ለሚያውቀው
ተናገረችና ፡ ልቧ ፡ በእርሱ ፡ ፀና [2]

ይረዳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይረዳል
ይረዳል ፡ የውጥን ፡ ይረዳል
የተዘጋን ፡ ከፍቶ ፡ በልጅ ፡ ይባርካል (፪x)

እስራኤላውያኖች ፡ ቀንበር ፡ ከብዶባቸው
የግብፅ ፡ ባርነት ፡ እጅግ ፡ ሰልችቷቸው
ጮሁ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዲታደጋቸው
እጁን ፡ ዘረጋና ፡ ነፃ ፡ አወጣቸው [3]

ያወጣል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያወጣል
ያወጣል ፡ ነፃነት ፡ ይሰጣል
ከእስራት ፡ ይፈታል ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

እመሰክራለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ
ንብ ፡ ማርን ፡ እንዲከብ ፡ ተከብቤ ፡ ሳለሁ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ አምላኬን ፡ ስጣራ
እርሱም ፡ ደረሰልኝ ፡ ጨለማዬም ፡ በራ

ያበራል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያበራል
ያበራል ፡ ጨለማን ፡ ይገፋል
በድንቅ ፡ ይደርስና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ ለሊትም ፡ በእሳት
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ መምራትን ፡ ሲያውቅበት
ላዘነው ፡ መፅናናት ፡ ለደካማው ፡ ብርታት
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላካችን ፡ እስኪ ፡ ዕልል ፡ በሉለት

ይብዛለት ፡ አሁንም ፡ ይብዛለት
ይብዛለት ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
አሜን ፡ ለአምላካችን ፡ ክብር ፡ ይሁንለት (፪x)

  1. ዘፍጥረት ፳፩ ፡ ፲፭ - ፲፱ (Genesis 21:15-19)
  2. ፩ ሳሙኤል ፩ ፡ ፲፪ - ፲፰ (1 Samuel 1:12-18)
  3. ዘፀአት ፫ ፡ ፩ - ፲፪ ፡ ፶ (Exodus 3:1-12:50)