ወንድሜ ፡ ንቃ (Wendemie Neqa) - ረዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ረዳ ፡ አብርሃም
(Redda Abraham)

Lyrics.jpg


(1)

አልጥልህም ፡ አልተውህም
(Altelehem Altewehem)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የረዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Redda Abraham)

አዝወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ጌታ ፡ እንደ ፡ ሌባ ፡ ይመጣልና
ቀን ፡ . (1) . ፡ አታውቅምና
ስለዚህ ፡ ንቃ ፡ መብራትህ ፡ ይብራ
በፍጻሜው ፡ ቀን ፡ እንዳትፈራ

አዝወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ስሙን ፡ በመፍራት ፡ ለሚኖሩት
የጽቅድ ፡ ጸሃይ ፡ ይወጣል ፡ በእውነት
እምላክህን ፡ ፍራ ፡ ጠብቀው ፡ ተግተህ
በክብር ፡ ሲገለጥ ፡ እንዳያፍርብህ

አዝወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ከማያምኑ ፡ ጋር ፡ ህብረት ፡ አይኑርህ
በማይመችህ ፡ መንገድ ፡ አትሂድ
ይልቅ ፡ ዘመኑን ፡ መርምር ፡ አጥብቀህ
በከንቱ ፡ አንዳያልፍ ፡ ጐልማሳነትህ

አዝወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ሰዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

እርሱን ፡ ከሚሉ ፡ ጋር ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ከሰው ፡ ሁሉ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ ይኑርህ
እጅጉን ፡ ንቃ ፡ ጊዜው ፡ ተቃርቧል
አሜን ፡ ይሆናል ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል

አዝወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ