ጥሬያለሁ ፡ ለአንተ (Terieyalehu Lante) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ጥሪያለሁ ፡ ለአንተ ፡ ጌት ፡ ኢየሱስ
ፊትን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)

በዓለም ፡ መኖርህ ፡ የታል ፡ ደስታህ
ነፍስህ ፡ እረፍትን ፡ መቼ ፡ አይታው
ተው ፡ ልብ ፡ ብለህ ፡ ስማኝ ፡ ወንድም
ልብህን ፡ አቀኝ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም (፪x)

አዝ፦ ጥሪያለሁ ፡ ለአንተ ፡ ጌት ፡ ኢየሱስ
ፊትን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)

ሰላም ፡ ነኝ ፡ ብትል ፡ ትዋሻለህ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ብትል ፡ ትቀጥፋለህ
ከጌታ ፡ እርቆ ፡ እረፍት ፡ የለም
ውስጥህ ፡ ያውጠንጥነው ፡ ተው ፡ ግድ ፡ የለም (፪x)

አዝ፦ ጥሪያለሁ ፡ ለአንተ ፡ ጌት ፡ ኢየሱስ
ፊትን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)

ብትራብ ፡ እንኳን ፡ ያጠግብሃል
ክፋትህን ፡ እንዲያይ ፡ መች ፡ ይወዳል
ፊትህን ፡ አዙረህ ፡ ስትሸሸው
እጁ ፡ እስኪያገባህ ፡ ትዕግስት ፡ አለው (፪x)

አዝ፦ ጥሪያለሁ ፡ ለአንተ ፡ ጌት ፡ ኢየሱስ
ፊትን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)


Navigation menu