Meserete Kristos Choir/Mesgana Melkam New/Mesgana Melkam New

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ዘማሪ መሠረተ ክርስቶስ መዘምራን አልበም ምሥጋና መልካም ነው Volume 5

አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ (፪x)

ሰናክሬም ጦር አሰልፎብኝ የማደርገው ምንም ሲጠፋኝ የምሥጋና መዝሙር ለጌታ ስዘምር ጠላቶቼን መታ አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ሌሊቱን በሙሉ ስለፋ አንድም የሚያዝ ዓሣ ጠፋ ታንኳዬን ለጌታ ስሰጠው መረቤን በዓሣዎች ሞላው አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ጳውሎስና ሲላስ በእስር ቤት ተጥለው ሳሉ በእስራት መዝሙር ሲዘምሩ ለጌታ የእጃቸው ሰንሰለት ተፈታ አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ክፉ ሰልጥኖበት ሳዖል ላይ አእምሮውን ስቶ ሲሰቃይ ዳዊት በገና ሲደረድር ክፉ መንፈስ ሸሸ ሲዘምር አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ሁሉን ለሚችለው ለኢየሱስ በእምነት አስረክቦ መፈወስ በምሥጋና ሆኖ መቆየት ባርኮት ይመጣል ከፀባኦት አዝ ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x) ሰዋለሁ ላምላኬ እልልታን ጨምሬ ለጌታ ስግደትን ጨምሬ (፪x)