ይህ ፡ ጌታ ፡ የማይረታ (Yeh Gieta Yemayereta) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ይህ ጌታ የማይረታ

 ልጆቹን አይጥልም ላንድ አፍታ

ይህን አይተናልና

ለእግዚአብሔር ምስጋና 2

 

    የእሳት ነበልባል ትንታግ ቢንቦለቦል

      ዙሪያችን ቢከበን የጥፋት ማዕበል

      እንደ ሲድራቅ ሚሳቅ እንደነ አብድናጎ

      የሱስ ያወጣናል በእጁ ፈልጎ

 

    በሰንሰለት ታስረው በወህኒ ሲጣሉ

      ሰማያዊ መዝሙር እያዜሙ ሳሉ

      የእስር ቤት መሠረት ያነቃነቀው ኃይል

      ዛሬም በዚህ ዘመን ሲሰራ አይተናል

 

    ዳዊት ከጠላቱ በጦር ሜዳ ቆሞ

      ጎልያድ ሲያቅራራ በወንጭፉ ቀድሞ

      አምላኩ እግዚአብሔርን በስሙ ጠራና

      በጠጠር ግምባሩን ጣለው በተነና

 

    በወንጌል ዘመቻ በመንፈስ መርምሮ

      የአጋንንትን ምሽግ በክንዱ ሰባብሮ

      የመረጣቸውን በፍጹም የማይጥል

 

      ዛሬም ሳይረታ እግዚአብሔር ይዋጋል


Navigation menu