መንገድ ፡ ዳር ፡ ቁጭ ፡ ብዬ (Menged Dar Quch Beyie) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ ሚመለከተኝ ሰው (2)ሲወለድ ጀምሮ አይኑ የታወረው (2)

       በጤናው አይደለም ኃጢአት ቢሠራ ነው ወይም በደል አለ ከዘር የወረሰው

      እያለ ሰው ሁሉ የሚፈርድብኝን ለምንም የማልሆን ከቶ የማልጠቅመውን

      በጉድፍ መጣያ የተቀመጥኩትን የክብርህ መግለጫ አደረከኝ እኔን (2)

 

    ደቀ መዛሙርቱ ግራ ቢገባቸው (2)እንዲህ እንዲወለድ ምክንያት የሆነው (2)

      እናት ወይስ አባት ከእነርሱ ማነው ወይስ እራሱ ነው ኃጢአት ያደረገው

      ብለው ሲያመነቱ የሚሉት ሲጠፋ በእኔ እንዲገለፅ የእግዚአብሔር ሥራ

      በምራቁ ጭቃ አይኖቼን ቀባና ታጠብ ብሎ ላከኝ ሰሊሆም ሂድና (2)

 

    ጨለማውን ገፎ ብርሃን ሲያደርግልኝ (2)ስድቤንና ነውሬን ሁሉ ሲያርቅልኝ (2)

      የአይኔን እውርነት የሱሴ ሲሽረው ያኔ እናት አባቴ አሉኝ ሙሉ ሰው ነው

      በቀድሞ ታሪኬ የሚያውቁኝ በሙሉ በእየሱስ ሥራ እጅግ ተገረሙ

      ሙሉ ሰው ላረገኝ ለዚህ ታላቅ ጌታ ምስጋናዬን ላቅርብ በሆታ በዕልልታ (2)


Navigation menu