ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (Oh Girum Hayl New) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ግሩም ሃይል ነው (2)

ጌታዬ ሆይ በክንድህ ውስጥ ያለው

ኦ ግሩም ሃይል ነው

 

    ፀሐይ ከዋክብትን በህዋ አንሳፈሃል

      መሬትን በተክል በውበት ፈጥረሃል

      ነፋስን በምድር ላይ እንዲሆን አዘሃል

      በውን ጌታዬ ሆይ ግሩም ሃይል ይዘሃል

 

    ላበቦች መዓዛን ለእንስሳት ማደሪያን

      ለኮከብ ጠፈርን ለአራዊትን ጫካን

      ለዓሣ ባህርን መኖሪያ አድርገሃል

      በውን ጌታዬ ሆይ ግሩም ሃይል ለብሰሃል

 

    ተራራ ሸንተረር ወንዝንም ሜዳንም

      ፈጥረሃል ጌታ ሆይ የሚሳንህ የለም

      ጥበብን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ሰጥተሃል

      በውን ጌታዬ ሆይ ግሩም ሃይል ይዘሃል


Navigation menu