ዕልልታ ፡ ነው (Elelta New) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እልልታ (3)

    እልልታ ነው እልልታ

ደስታ ታላቅ ደስታ

በቤተልሔም ተወልዷል ጌታ እልልታ (4)

 

    በነብዩ አንደበት እግዚአብሔር ተናግሮ

      በዛብሎን ምድር ገሊላን ተሻግሮ

      የሃጢአት ጨለማ ግርዶሹን ለመግፈፍ

      በሞት ጥላ ሃገር ብርሃኑን ሊያሰርፍ የሱስ አለ ከተፍ

 

    እረኞች በሌሊት ሳሉ ከመንጋቸው

      የእግዚአብሔር ክብር ሲያበራ ዙሪያቸው

      ታላቅ የምስራች ከመላኩ ሰሙ

      ከነገሥታት ይልቅ እረኞች ታደሙ ከሄሮድስ ቀደሙ

 

    ከሩቅ ምስራቅ መጡ ጠቢባን ተጉዘው

       ወርቅና እጣን ከርቤ ሊሰግዱለት ይዘው

       ተንበረከኩለት ቤትልሔም ደመቀች

       በኢየሱስ መወለድ የጽድቅ ፀሐይ ታየች ነፍሳችን አረፈች

 

    ኢየሱስ እንዲሉት ስሙ ተሰጣቸው

       ህዝቡን ከሃጢአት ሁሉ ሊያድናቸው

       ማንም ቢወድ መጥቶ ከሃጢአት ይፈታ

 

       መላዕከትም በሰማይ ያሰሙ ደስታ በምድርም እልልታ


Navigation menu