ክብር ፡ ይሁንለት (Keber Yehunelet) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ክብር ይሁንለት(4) አማኑኤል መጥቷል
የፍቅር የሰላምየአንድነት መሠረት
ክብር ይሁንለት

አምላክ በሰው አድሮ በቅድስተ ድንግል
ከክብሩ ተዋርዶ ሊያነጻን ከበደል
የአንድነት መሰረት መድኃኒተ ዓለም
ተወልዷል ከፍ ይበል እናውጅ ለዓለም (2)

አዝ፦ ክብር ይሁንለት(4) አማኑኤል መጥቷል
የፍቅር የሰላምየአንድነት መሠረት
ክብር ይሁንለት

የዳዊት ከተማ ቤተልሔሚቱ
በአንቺ የተወለደው ንጉሠ ነገሥቱ
ዛሬም በምድር ዙሪያ ይሰማል አዋጁ
በኃጢአት የተዘጋው እንዲከፈት ደጁ (2)

አዝ፦ ክብር ይሁንለት(4) አማኑኤል መጥቷል
የፍቅር የሰላምየአንድነት መሠረት
ክብር ይሁንለት

የሃጢአት ቀንበር ጫንቃችን ተጭኖት
ተስፋችን ጨልሞ ከቦን የሞት ፍርሃት
ጽድቅን አልባሻችን የደካሞች ጉልበት
የሱስ ተወለደ ክብር ይሁንለት (2)

አዝ፦ ክብር ይሁንለት(4) አማኑኤል መጥቷል
የፍቅር የሰላምየአንድነት መሠረት
ክብር ይሁንለት

በዝሙት በስካር በነፍስ ገዳይነት
በህመም በደዌ ታስራችሁ በሃጢአት
የተቸገራችሁ ጠፍቷችሁ መንገዱ
ወደ የሱስ ኑና ዳግም ተወለዱ (2)

አዝ፦ ክብር ይሁንለት(4) አማኑኤል መጥቷል
የፍቅር የሰላምየአንድነት መሠረት
ክብር ይሁንለት


Navigation menu