ኢየሱስ ፡ ገብቶ ፡ በሕይወቴ (Eyesus Gebto Behiwote) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ኢየሱስ ገብቶ በህይወቴ
ወዲያው ለወጠው ማንነቴን
ፍቅሩ ጥልቅ ነው (3)
ፍፁም አልችልም ልገልፀው
የእየሱስ ፍቅር ጥልቅ ነው

ጌታ በፍቅሩ እኔን ለወጠኝ
አዲስም ፍጥረት አረገኝ
ረቂቅ በሆነው መንፈሱ
አረጋት ነፍሴን ለራሱ (2)

አዝ፦ ኢየሱስ ገብቶ በህይወቴ
ወዲያው ለወጠው ማንነቴን
ፍቅሩ ጥልቅ ነው (3)
ፍፁም አልችልም ልገልፀው
የእየሱስ ፍቅር ጥልቅ ነው

ውስጤን ያላዩ ማንነቴን
ካድ እንኳን ቢሉኝ እምነቴን
አልችልም ፍጹም ልለየው
የየሱስ ፍቅር ጥልቅ ነው (2)

አዝ፦ ኢየሱስ ገብቶ በህይወቴ
ወዲያው ለወጠው ማንነቴን
ፍቅሩ ጥልቅ ነው (3)
ፍፁም አልችልም ልገልፀው
የእየሱስ ፍቅር ጥልቅ ነው

ሲቃ የያዘው ጣር ጩኸት
ራሱን እስከ ሞት የሰጠበት
ምን አይነት ጠሊቅ ፍቅር ነው
የእኔን ድንጋይ ልብ ለወጠው

አዝ፦ ኢየሱስ ገብቶ በህይወቴ
ወዲያው ለወጠው ማንነቴን
ፍቅሩ ጥልቅ ነው (3)
ፍፁም አልችልም ልገልፀው
የእየሱስ ፍቅር ጥልቅ ነው


Navigation menu