ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው (LeEgziabhier Qelal New) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ይህም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ቀላል
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው (፪x)

ቀላል ፡ ነው ፣ ቀላል ፡ ነው (፪x)

ከባድ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
ትልቅ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
አስፈሪ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
አልችልም ፡ የሚል ፡ ቃልን ፡ አታውቅም

ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እደሰታለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጸልያለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አከብርሃልሁ

አመልክሃለው ፣ አመልክሃለው (፪x)

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ መልሱን ፡ የነገርከኝ
ምንም ፡ እንዳይመስለኝ ፡ ያደረከኝ
እስከሚገርመኝ ፡ ድርስ ፡ እደሰታለሁ
ከባዱ ፡ ፈተና ፡ ለካ ፡ ቀላል ፡ ነው

ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ምንም፡ ነው ፡ ምንም
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ምንም ፡ ነው
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ቀላል
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው

ቀላል ፡ ነው ፣ ቀላል ፡ ነው
ምንም ፡ ነው ፣ ምንም ፡ ነው

ከባድ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
ትልቅ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
አስፈሪ ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
ምንም ፡ መጣ ፡ ብለህ ፡ አትደነግጥም

ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እደሰታለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጸልያለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቅሃለሁ

አመልክሃለው ፡ አከብርሃለሁ
እደሰታለሁ ፡ እጸልያለሁ

የለም ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
አልቋል ፡ የሚባል ፡ ነገር ፡ አታውቅም
አልችልም ፡ የሚል ፡ ቃልን ፡ አታውቅም
አይሆንም ፡ የሚል ፡ ቃልን ፡ አታውቅም

ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አከብርሃልሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እደሰታለሁ
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጸልያለሁ

እጸልያለሁ ፡ አከብርሃልሁ
እጠብቃለሁ ፡ እደሰታለሁ

ይህም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ቀላል
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ቀላል ፡ ነው
ይህም ፡ በአምላኬ ፡ ዓይን ፡ ምንም፡ ነው ፡ ምንም
ይህም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዓይን ፡ ምንም ፡ ነው
ኧረ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ምንም ፡ ነው ፡ ምንም
ኧረ ፡ በአምላኬ ፡ ምንም ፡ ነው

ምንም ፡ ነው ፣ ምንም ፡ ነው (፪x)
ቀላል ፡ ነው ፣ ቀላል ፡ ነው (፪x)


Navigation menu