Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Chelemayen Geta Eyabera
ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ሌላ ሥም ሊሊ ርዕስ ጨለማዬን ጌታ እያበራ አልበም ጨለማዬን ጌታ እያበራ
ጨለማዬን ጌታ እያበራ በእሳት በደመና እየመራ ክፉ በሆኑብኝ ቀኖች ፈንታ ደስታን አጠገበኝ የኔ ጌታ
ምን እላለሁ ምስጋናን ተሞልቻለሁ ምን እላለሁ ጌታ አምላኬን አከብራለሁ
አንተ ለኔ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው በጎነትህ /ቸርነትህ/ አያልቅም ባወራው ብዘምረው
የፊቱ ብርሃን አበራልኝ በልቤም ደስታን ጨመረልኝ ጌታ ምህረቱ እረድቶኛል ሃዘኔን ችግሬን አስትቶኛል (2x)
ምን እላለሁ ምስጋናን ተሞልቻለሁ ምን እላለሁ ጌታ አምላኬን አከብራለሁ
አንተ ለኔ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው በጎነትህ/ቸርነትህ አያልቅም ባወራው ብዘምረው
ለልቤ እንደመከራዋ ብዛት ማፅናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት እግዚአብሔር ከላይ አስቦኛል በዘመኔ ሁሉ ደስ ይለኛል (2x)
ምን እላለሁ ምስጋናን ተሞልቻለሁ ምን እላለሁ ጌታ አምላኬን አከብራለሁ
አንተ ለኔ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው በጎነትህ/ቸርነትህ/ደግነትህ/ፍቅርህም አያልቅም ባወራው ብዘምረው