ያለምህረትህ (Yalemehereteh) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬x)
ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፮x)

የምህረት ፡ ደጆችህ ፡ ተከፍተውልኛል
እጅህም ፡ ለእኔ ፡ ተዘርግቶልኛል
(፪x)
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ

ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬x)

የእኔ ፡ መታመኛ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ ፡ ነው
ድፍረት ፡ የሚሰጠኝ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህ ፡ ነው
(፪x)
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)

ኢየሱስ ፡ መባና ፡ መሰዋእት
ኢየሱስ ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ
ኢየሱስ ፡ አድርጐ ፡ እራሱን
ኢየሱስ ፡ የሰጠኝ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ
ኢየሱስ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ማታ

የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ
የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አምላክና ፡ አባት ፡ ይባረክ
የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ
የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አባትና ፡ አምላክ ፡ ይባረክ

ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፭x)


Navigation menu