አባባ (Ababa) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ የሚመሩ ፡ እነዚህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ናቸው።
ይላል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል።
ታዲያ ፡ አንድ ፡ ማለዳ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ሳለሁኝ
ጌታን ፡ በውስጤ ፡ የተሞሉትን ፡ ጥያቄዎች ፡ ለመጠየቅ
እየተዘጋጀሁኝ ፡ እንደዚህ ፡ እያልኩት ፡ ነበረ።
እነዚህን ፡ ጥያቄዎች ፡ በዝማሬ ፡ እነግራቹሃለሁ ፤
በመጀመሪያም ፡ እንደዚህ ፡ ስል ፡ ጠየኩት።

አዝ፦ አባባ ፡ አባ ፡ አባባ (፪x)
የልጅህን ፡ ጩኸት ፡ ስማ (፪x)

ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ

ልጄ ፡ እኔም ፡ እሰማሃለሁ
ሳትጠይቀኝ ፡ እረዳለሁ
ብረሳህ ፡ ቀኜ ፡ ትርሳኝ
ብተውህ ፡ አያስችለኝም
አንዳንዴ ፡ ስለምንህ ፡ አትሰማኝም
ስጠይቅህ ፡ ቶሎ ፡ አትሰጠኝም
ለምንድነው ፡ አባ ፡ ምትከለክለኝ
እጅህን ፡ ሰብስበህ ፡ ዝም ፡ የምትለኝ

ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በሚያባብል ፡ ቃሎቹ ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ

ልጄ ፡ መች ፡ ሁሉ ፡ ይጠቅምሃል
አንዳንዱ ፡ እኮ ፡ ይጐዳሃል
አንተ ፡ ስለማታውቀው ፡ ነዉ
መች ፡ መሰለህ ፡ አምሮህ ፡ ብታየው
ስከለክልህ ፡ አይክፋህ
አትፍጠን ፡ ቶሎ ፡ ለኩርፊያ
ጠላት ፡ ይህንን ፡ አይቶ
በኩርፊያህ ፡ ደስ ፡ አታሰኘው
እንደሳሙኤል ፡ አባ ፡ እኔንም ፡ ጥራኝ
ድምጽህን ፡ ለይተህ ፡ አሳውቀኝ
የኤሊ ፡ ድምጽማ ፡ መቼ ፡ ይጠቅመኛል
እንደራሱ ፡ ልጆች ፡ ያበላሸኛል

አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ በፍቅር ፡ መናገር ፡ ሲችል ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ ተናገረ

ልጄ ፡ ለሰዎች ፡ ድምጽማ ፡ እኔ ፡ መች ፡ እተውሃለሁ
እንደ ፡ መልካም ፡ እርሻ ፡ ሁሌ ፡ እኮተኩትሃለሁ
የጽድቅ ፡ ቡካያዬ ፡ ነህ ፡ ፍሬህን ፡ አበዛዋለው
ዘርህን ፡ እንደከዋክብት ፡ ምድርን ፡ እሞላታለሁ
አዝ፦ አባባ ፡ አባ ፡ አባባ (፪x)
የልጅህን ፡ ጩኸት ፡ ስማ (፪x)

ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ

ልጄ ፡ እኔም ፡ እሰማሃለሁ
ሳትጠይቀኝ ፡ እረዳለሁ
ብረሳህ ፡ ቀኜ ፡ ትርሳኝ
ብተውህ ፡ አያስችለኝም
የኤልዛቤል ፡ ዛቻ ፡ አስፈርቶኝ
ከክትክታው ፡ ዛፍ ፡ ስር ፡ ወድቂያለሁኝ
ረሃቡ ፡ ጸንቶብኝ ፡ ቶሎ ፡ ሳይገድለኝ
አባ ፡ በጊዜ ፡ ና ፡ ቶሎ ፡ መግበኝ

ጌታም ፡ በፍቅር ፡ ቃሎቹ ፡ እየደጋገመ ፡ ይናገረኝ ፡ ቀጠለ

ከሰማይ ፡ መልአኬን ፡ ልኬ ፡ ልጄ ፡ እኔ ፡ እመግብሃለሁ
ሁሉ ፡ የሞላኝ ፡ አባትህ ፡ እኔ ፡ ለአንተ ፡ መቼ ፡ እሰጥህሃለሁ
ዳቦ ፡ ስትለምነኝ ፡ ድንጋይ ፡ ዓሣ ስትለምን ፡ እባብን
እኔ ፡ መች ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ልጄ ፡ አንተን ፡ የሚጐዳህን
ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ መርጠህ ፡ የለየኸኝ
ሰልችተህ ፡ ጣል ፡ ጣል ፡ ተው ፡ አታድርገኝ
አንተ ፡ የጣልከኝ ፡ እለት ፡ ጉዴ ፡ ይፈላል
ያለ ፡ አንተስ ፡ እኔ ፡ መች ፡ ያምርብኛል

የፍቅር ፡ ቃሎች ፡ የሞሉት ፡ ጌታ ፡ ደግሞ ፡ እንደዚህ ፡ ብሎ ፡ ተናገረኝ

እናት ፡ እንኳ ፡ ልጇን ፡ ረስታ
ምናልባት ፡ ትጥል ፡ ይሆናል
ልጄ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አልረሳህም
ያለ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ አይሆንልኝም
እጅና ፡ እግሬ ፡ የቆሰለልህ
የደሜ ፡ ካሳ ፡ የሆነህ
ልጄ ፡ ልጥልህ ፡ ባስብም
አንጀቴ ፡ እኮ ፡ አይችልልኝም
አዝ፦ የምትወደኝ ፡ አባባ (፪x)
ምሥጋናዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው
ዕልልታዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው

ምሥጋና ፡ ልቤን ፡ በሞላው ፡ ጊዜ ፡ ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ እያለ ፡ መናገር ፡ ጀመረ

ልጄ ፡ ፈጥኜ ፡ እመጣለሁ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ አኖርሃለሁ
እምባ ፡ ያራሰው ፡ ፊትህን
ያኔ ፡ እኔ ፡ አብሳለሁኝ
አዝየምትወደኝ ፡ አባባ (፪x)
ምሥጋናዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው
ዕልልታዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው