ክብር ፡ ይገባሃል (Keber Yegebahal) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እግዚአብሔር ፡ ነገሠ ፡ ክብር ፡ ለበሰ
ታጠቀ ፡ ኃይልንም ፡ ለበሰ
ዓለምን ፡ አጸናት ፡ አቆማት
ምሕረቱም ፡ ድንቅ ፡ ዘለዓለማዊ

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ

ዘለዓለማዊ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
ዝግጁ ፡ ነው ፡ ከጥንት ፡ ዙፋንህ
. (2) .
፡ ከፍ ፡ አደረጉ ፡ ድምጻቸውን
ተራሮች ፡ ፡ ፡ ፡ ሰጡህ ፡ ክብርን

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ

ከብዙ ፡ ውሃዎች ፡ ድምጽ ፡ ይልቅ
ከታላቅ ፡ ሞገድም ፡ ድምጽ ፡ ይልቅ
ጌታችን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኃያል ፡ ድንቅ
ምስክር ፡ ታማኝ ፡ አንተ ፡ ታላቅ

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ


Navigation menu