ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (Del Bedel Godana) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 2:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x)

ያን ድቅድቅ ጨለማ የሞትን ሸለቆ
ታገለው ክርስቲያን የእምነት ትጥቁን ታጥቆ
አሻፈረኝ ብሎ ለእርሱ ላይረታ
በድል ጥሎት ወጣ በጌታው መከታ

አዝ:- ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና
ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x)

የጥሻው ጨለማ ብርሃን ወጣበት
ክርስቲያን በእምነት ሰይፍ አንዴ ቢዘምትበት
የማጥመጃው ሜዳ በደም አጥለቅልቆ
ሕይወትን ዘራበት እንዲበቅል አውቆ

አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና
ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x)

ጋሻ ጦሩ መንፈስ ፍላጻው እምነቱ
ማን ሊቋቋመው ያን ክንደ ብርቱ
ሊያጠምዱት ሊያስቀሩት አጥብቀው ቢጥሩ
ከአምላኩ ደም ቅጥር አልነቀለም እግሩን

አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና
ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x)