ልመለስ (Lemeles) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

በአንተ ፡ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ባባቴ ፡ ቤት ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ
ተትረፍርፎ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ጠፍቶ
ከሱ ፡ ላይ ፡ አይኔ ፡ ተነሳ
ላይጠቅመው ፡ ሌላውን ፡ አይቶ
የእራሴ ፡ መንገድ ፡ አጠፋኝ ፡ ተጎዳሁኝ
ሆ ፡ ከርያ ፡ ለመዋል ፡ ተገደድኩኝ
ዛሬ ፡ ፍቅሩን ፡ ናፍቄያለሁ ፡ እመለሳለሁ
ሆ ፡ እንደልጅ ፡ ባልሆን ፡ ባሪያ ፡ ሆናለው

አዝ፦ ያለሱማ ፡ ኑሮ ፡ እንደማይሆን ፡ ተረዳሁ
አሁን ፡ ይብቃኝ ፡ ምንም ፡ ላላተርፍ ፡ ተጎዳሁ
ልመለስ ፡ የቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ ይሻለኛል
ሆ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይመቸኛል
የዓለም ፡ ኑሮ ፡ አንገፍግፎኛል ፡ ብዙ ፡ አራቅቶኛል
ሆ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ፡ እርሱ ፡ ይሻለኛል

መስሎኝ ፡ ነበር ፡ የተጠቀምኩ
ድርሻዬን ፡ ይዤ ፡ ኮበለልኩ
ሀብቴን ፡ በሜዳ ፡ በተንኩኝ
አይ ፡ ሞኙ ፡ መች ፡ አስተዋልኩኝ
ያባቴን ፡ ምክር ፡ ሳልሰማ ፡ በመቅረቴ
ሆ ፡ ረሃብ ፡ ጎዳኝ ፡ ተጣብቆ ፡ አንጀቴ
ልመለስ ፡ ፊቱን ፡ ለማየት ፡ ብዙም ፡ ባልደፍርም
ሆ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከቶ ፡ አይገኝም

ገንዘብ ፡ አላፊ ፡ ጠፊ ፡ ነው
ሰው ፡ ድጋፍ ፡ አይሆን ፡ ሸምበቆ ፡ ነው
ልጅነቴ ፡ አታለለኝ
አርቆ ፡ አለማሰቤ ፡ ጎዳኝ
ዛሬስ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ምህረት ፡ ናፍቄያለሁ
ሆ ፡ አይጨክንም ፡ ይኸን ፡ አውቃለሁ
ጉስቁልናዬንም ፡ አይቶ ፡ ያዝንልኛል
ሆ ፡ ውዱ ፡ አባቴ ፡ ይቅር ፡ ይለኛል

አዝ፦ ያለሱማ ፡ ኑሮ ፡ እንደማይሆን ፡ ተረዳሁ
አሁን ፡ ይብቃኝ ፡ ምንም ፡ ላላተርፍ ፡ ተጎዳሁ
ልመለስ ፡ የቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ ይሻለኛል
ሆ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይመቸኛል
የዓለም ፡ ኑሮ ፡ አንገፍግፎኛል ፡ ብዙ ፡ አራቅቶኛል
ሆ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ፡ እርሱ ፡ ይሻለኛል

መድኔ ፡ ጋር ፡ እመለሳለው
ሀዘኔን ፡ በዚያ ፡ ረሳለው
ጉስቁልናዬም ፡ ይቀራል
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ይራራል
ያደፈ ፡ ልብሴን ፡ አውልቆ ፡ ሌላ ፡ ያለብሰኛል
ሆ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩን ፡ ይመግበኛል
መንፈሱን ፡ ያፈስልኛል ፡ እፅናናለው
ሆ ፡ ለዘላለም ፡ በርሱ ፡ አርፋለው

አዝ፦ ያለሱማ ፡ ኑሮ ፡ እንደማይሆን ፡ ተረዳሁ
አሁን ፡ ይብቃኝ ፡ ምንም ፡ ላላተርፍ ፡ ተጎዳሁ
ልመለስ ፡ የቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ ይሻለኛል
ሆ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይመቸኛል
የዓለም ፡ ኑሮ ፡ አንገፍግፎኛል ፡ ብዙ ፡ አራቅቶኛል
ሆ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ፡ እርሱ ፡ ይሻለኛል