እንዳንተ ፡ የለም (Endante Yelem) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ የነገስታት ፡ ንጉስ
የሚመስልህ ፡ የሌለህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እየሱስ

አመልክሃለሁ/4X/

መጥቻለሁ ፡ በፊትህ ፡ ላመልክህ ፡ ነው
አስቀድሜ ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ እሰግዳለው
ቀና ፡ ብዬ ፡ አንተን ፡ ሳይ ፡ ተውበሃል
የምስጋናን ፡ የክብርን ፡ ዘውድ ፡ ጭነሃል

እጨምራለው ፡ በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ንጉሴ ፡ ሆይ
ከዚህም ፡ በላይ ፡ ንገስ ፡ ባማረ ፡ ዜማ
በተዋበ ፡ እልልታ ፡ ይድመቅ ፡ ዙፋንህ
ተመለክ ፡ ተውደስ ፡ የኔ ፡ ጌታ

እኔም ፡ አላውቅህም ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ ማንነትህ /2X/

ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ የተቀመጥቀው
ብርሃንን ፡ እንደ ፡ ልብስ ፡ የለበስከው
ማዕረግህ ፡ ስልጣንህ ፡ የብቻህ ፡ ነው
በሹመትስ ፡ የተሾመ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

እጨምራለው ፡ በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ንጉሴ ፡ ሆይ
ከዚህም ፡ በላይ ፡ ንገስ ፡ ባማረ ፡ ዜማ
በተዋበ ፡ እልልታ ፡ ይድመቅ ፡ ዙፋንህ
ተመለክ ፡ ተውደስ ፡ የኔ ፡ ጌታ

እኔም ፡ አላውቅህም ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ ማንነትህ /2X/

በክብር ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ክቡር ፡ ማነው
ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በሞገስ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ሞገሳም ፡ ማነው
ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በሀይል ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ሀያል ፡ ማነው
ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በስልጣን ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ባለስልጣን ፡ ማነው
ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በአማልክት ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ አምላክ ፡ ማነው
ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በፍጹም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም/2X/
አይኖርም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም/2X/