አይችልም ፡ ሊደበቅ (Ayechelem Lidebek) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

Lyrics.jpg


(2)

እርስ ፡ አልቀይርም
(Erese Alekyerem)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

አይችልም ሊደበቅ ብርሃን ነው ያለው ውስጤ
ኧረ አይችልም ሊደበቅ መድሃኒት ነው ያለው ውስጤ
ኧረ አይችልም ሊደበቅ እየሱስ ነው ያለው ውስጤ
ኧረ አይችልም ሊደበቅ ቅባቱ ነው ያለው ውስጤ

አይችልም ሊደበቅ ብርሃን አለ በውስጤ
አይችልም ሊደበቅ መድሃኒት አለ በውስጤ
አይችልም ሊደበቅ እየሱስ አለ በውስጤ
አይችልም ሊደበቅ ቅባቱ አለ በውስጤ

የሚፈውስ ነው የሚያድን
ነጻ ሚያወጣ ነው በኔ ውስጥ ያለው/2

አደረገኝ ከሁኔታ በላይ አደረገኝ
አደረገኝ ከሚሰማው በላይ አደረገኝ
አደረገኝ ከከፍታም በላይ አደረገኝ
አደረገኝ ከዝቅታም በላይ አደረገኝ

የእግዚአብሔር ሃይል የሆነው ሁሉን ሚፈጥረው
ክርስቶስ እየሱስን ደግሞ ከሞት ያስነሳው
ያመንፈስ በኔ ውስጥ ዛሬም ህያው ሆኖ ይሰራል
ከጨለማው አለም ብርሃን እንድሆን አርጎኛል

እኔን የነካ ያይኑን ብሌን ነካ እኔን የነካ
እኔን የነካ እየሱስን ነካ እኔን የነካ
እኔን የነካ ማደሪያውን ነካ እኔን የነካ
እኔን የነካ መቅደሱን ነካ እኔን የነካ

አይችልም ሊደበቅ ብርሃን አለ በውስጤ…

የሚፈውስ ነው የሚያድን…

አደረገኝ ከሁኔታ በላይ አደረገኝ…

ከከበበኝ በላይ ከሁኔታ በላይ
ካስጨናቂው በላይ አደረገኝ /2

ውስጤ ያለው መንፈስ ከሃይሉ ከክብሩ የተነሳ
እባብራ ጊንጡን እንድረግጠ በእግሬ ስር አስገዛ
ባለም ካለው በላይ በኔ ውስጥ ያለው ታላቅ ነው
የሁሉ መዳኒት መፍትሔ አርሱ ብቻ ነው

ክብር አለኝ እኔ ማደሪያው ላረገኝ
ክብር አለኝ እኔ መቅደሱ ላደረገኝ/2