Awtaru Kebede/Yeqerta/Egziabhier Sinager

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ አውታሩ ከበደ ርዕስ እግዚአብሔር ሲናገር አልበም ይቅርታ

እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ አንድ ነገር ሁሉንም ይችላል እኔ ዝም ልበል አምላኬ ሲናገር ሰማሁ አንድ ነገር ኃይል የእግዚአብሔር ነው ምድር ዝም ትበል

ይችላል እግዚአብሔር ቋጠሮዬን መፍታት ይችላል እግዚአብሔር የሞተ ማስነሳት (፪x)

ሞቷል ወይ ቀበርከው ወይ ዛሬ ቀኑ ነው (፫x) ክብሩን ልታይ ቀኑ ነው ክብሩን ልታይ (፬x)

አረጀ አብርሃም ደከመ ጉልበቱ ዛሬማ አይደለም እንደ ልጅነቱ አበቃ ተቆርጧል የእርሱ ነገርማ ምድር ተገረመች መውለዱ ሲሰማ ምንም በሌለበት ጭር ባለው ቦታ አንድ ብሎ ጀመረ ሁሉን ቻዩ ጌታ

ይችላል እግዚአብሔር ቋጠሮዬን መፍታት ይችላል እግዚአብሔር የሞተ ማስነሳት (፪x)

ብቻ ይናገረኝ ቃል ይዉጣ እንጂ ከአፉ እጠብቀዋለሁ ቀኑ ቢሆን ክፉ በገናን አልሰቅልም እደረድራለሁ ከሁኔታ በላይ አባቴ ትልቅ ነው አባቴ ትልቅ ነው ከሁኔታ በላይ በእርሱ ለታመኑ/ታምኛለሁ/ጤና ይስጥልኝ እና ይፈርዳል ከሰማይ (፪x)

እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ አንድ ነገር ሁሉንም ይችላል እኔ ዝም ልበል አምላኬ ሲናገር ሰማሁ አንድ ነገር ኃይል የእግዚአብሔር ነው ምድር ዝም ትበል

ይችላል እግዚአብሔር ቋጠሮዬን መፍታት ይችላል እግዚአብሔር የሞተ ማስነሳት (፪x)

ሞቷል ወይ ቀበርከው ወይ ዛሬ ቀኑ ነው (፫x) ክብሩን ልታይ ቀኑ ነው ክብሩን ልታይ (፬x)

የማሰሮው ዘይት የማድጋው ዱቄት አንድ ቀን ብቻ ነው ነገ የለም ሕይወት እያለች ተጨንቃ ከአንድ ልጇ ጋራ እግዚአብሔር አሰባት መጣ የእርሷ ተራ ዝናብ እስኪመጣ ምድር እስኪያበቅል በበረከት ሞላው ቤቷን በሰላም

ይችላል እግዚአብሔር ቋጠሮዬን መፍታት ይችላል እግዚአብሔር የሞተ ማስነሳት (፪x)