ሄደ ፡ ወደ ፡ አምላኩ (Hiede Wede Amlaku) - አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

1
(1)

ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአገኘሁ ፡ ይደግ ፡ እና ፡ እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Agegnehu Yideg and Endale Woldegiorgis)

ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ
ኢየሱስን አምኖ አለምንየካደ
ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ

ሄደ ወደ አባቱ ሄደ
ኢየሱስን አምኖ አለምንየካደ
ሄደ ወደ አባቱ ሄደ

1 ከዚህ አለም ክብር ኢየሱስ ይበልጣል ህይወትን ይሰጣል
ብሎ እየሰበከ ለትንሽ ትልቁ ከእግዚአብሔር ታረቁ
የአለምን ፈተና የስጋውን ምኞት ሁሉን አሸንፎ
ሄደ ወደ አምላኩ ወገቡ ሳይላላ ፀጋውን ተደግፎ
 
ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ
ኢየሱስን አምኖ አለምንየካደ
ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ

ሄደ ወደ አባቱ ሄደ
ኢየሱስን አምኖ አለምንየካደ
ሄደ ወደ አባቱ ሄደ

2 ከባልንጀሮቹ ከቤተ ዘመዱጌታን አስበልጦ
ሄደ ወደ አምላኩ ግንባሩን ሳያጥፍ የህይወት መንገድ መርጦ
በበጉ ዙፋን ፊት ሁሉም ሲሰበበሰብ የእርሱ ስም ይጠራል
ከቅዱሳን ጋራ እንደሰማይ ፀዳል ዘላለም ያበራል

ሄደች ሄደች ወደ አባቷ ሄደች
ኢየሱስን ብላ አለምን የካደች
ሄደች ወደ እረፍቷ ሄደች

ሄደች ሄደች ወደ ኢየሱስ ሄደች
እግዚአብሔርን አምና አለምን የካደች
ሄደች ወደ ደስታዋ ሄደች

3የፍጥረት ሩጫ አንድ ቀን ይገታል ሰማይ ምድር ያልፋል
የጌታን ቃል ሰምቶ ከመርከቡ የገባ ከቁጣው ይተርፋል
የሰው ልጅ ሞኝ ነው በሀብት በስልጣኑ በእውቀቱ ይደገፋል
በድንገት አንድ ቀን እግዚአብሔር ሲጠራው ሁሉን ትቶት ያልፋል

ሄደች ሄደች ወደ ኢየሱስ ሄደች
እግዚአብሔርን አምና አለምን የካደች
ሄደች ወደ ደስታዋ ሄደች

ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ
ኢየሱስን አምኖ አለምንየካደ
ሄደ ወደ አምላኩ ሄደ