ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (Gietayien Akebralehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

አነባ ፡ ጌታዬ ፡ አፈር ፡ ላይ ፡ ተደፍቶ
የወደቀበትን ፡ ጭንቀት ፡ ተመልክቶ
ጌታዬ ፡ ተጨንቆ ፡ አባዬ ፡ ሆይ ፡ አለ
አጋዥ ፡ አልተገኘም ፡ ለጌታ ፡ የዋለ

መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ትከሻው ፡ ተላጠ
ግርፋቱ ፡ በዛ ፡ ገላው ፡ ተመለጠ
ራቁቱን ፡ ደም ፡ ሲያፈስ ፡ በቀራንዮ ፡ ዋለ
አንገቱ ፡ ደፋ ፡ ሲል ፡ እዳ ፡ ተከፈለ

አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x)
ዝናን ፡ ከበሬታን ፡ ሞገስን ፡ በሥጋ
ሊያገኝ ፡ ወዶ ፡ ነፍሱን ፡ ከአለም ፡ ከሚያስጠጋ
ይሻላል ፡ ጭንጋፉ ፡ ውዳቂ ፡ እኔን ፡ መሳይ
በስጋው ፡ ተንቆ ፡ በእምነት ፡ ጌታን ፡ የሚያይ<፪>
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x)

ማቅቆ ፡ በመከራ ፡ ጐስቋላ ፡ አካል ፡ ይዞ
በረሃን ፡ የሚዘልቅ ፡ ጌታን ፡ ተመርኩዞ
ተሽማቆ ፡ ኑሮን ፡ ለጌታ ፡ ሲል ፡ ችሎ
ያለፈን ፡ አየሁት ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ

አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x)

በሞቱ ፡ ሊመስለው ፡ ጌታን ፡ ተከትሎ
ወድቆም ፡ የሚነሳ ፡ አልሸነፍ ፡ ብሎ
ለጠላቱ ፡ ታግሎ ፡ የማታ ፡ የማታ
ጌታው ፡ ምሎለታል ፡ እርሱ ፡ እንደሚረታ

አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፬x)