እረኛዬ ፡ መከታዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሳዝን ፡ ስንገላታ ፡ ጠላትም ፡ ሲያጠቃኝ ፈተና ፡ ሲከበኝ ፡ ቀን ፡ ሲጨልምብኝ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ልትረዳኝ ፡ የምትችል ተስፋዬ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ሌላማ ፡ የለኝም

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ። 
።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ።  ። 

ደግፈኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ተራመድ አላፊውን ፡ ደስታ ፡ ልቦናዬ ፡ እንዳይወድ

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

ስማኝ ፡ አፍቃሪዬ ፡ ስሞታዬን ፡ እንካ ልቤ ፡ እንዳዘነብኝ ፡ ልብህም ፡ ይነካ ሌላማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ቋሚ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ሃዘኔ ፡ ሚሰማው ፡ ልቡ ፡ የሚራራ

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

ሥጋ ፡ ደካማ ፡ ነው ፡ ሁሉንም ፡ ይመኛል ስሜትም ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ ከውድቀት ፡ ያደርሳል ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ውድቀት ፡ ጠብቀኝ ፡ ጌታዬ እምነቴ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ጥብቅ ፡ ነው ፡ መሪዬ