Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Demun Lenie Afeso

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኮብልላ ፡ ነበረች ፡ ነፍሴ ፡ ከእግዜር ፡ መንገድ
በጣም ፡ የበደልኩኝ ፡ ኃጢአተኛም ፡ ነበርኩ
ግን ፡ አዳኜ ፡ ከላይ ፡ ፍቅሩን ፡ ሰጠኝ ፡ ሰላም
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን
አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ነበርኩኝ ፡ ሊያወጣኝ ፡ ሲመጣ
ግን ፡ እርሱ ፡ ነገረኝ ፡ ነጻ ፡ እንደምወጣ
ከዚያማ ፡ አነሳና ፡ ክብሩን ፡ አቀዳጀኝ
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን
አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፡ ከመረጥኩት ፡ ወዲህ
ከማዕበሉ ፡ አሁን ፡ ወደርሱ ፡ ሸሻለሁ
ክንዱን ፡ ከተደገፍኩ ፡ አልፈራም ፡ መከራን
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን
አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ

ሰማያዊ ፡ ደስታን ፡ ሰላምን ፡ ከሰጠኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ለአንተ ፡ ሰጣለሁኝ
እንግዲህ ፡ እጄን ፡ ያዝ ፡ ከአንተም ፡ ጋር ፡ አቁመኝ
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ

ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን
አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ