Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Tez Yelegnal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{Lyrics | ርዕስ = ትዝ ፡ ይለኛል | Title = Tez Yelegnal | ዘማሪ = አዲሱ ፡ ወርቁ | Artist = Addisu Worku | Volume = 1 | አልበም = ክቡር ፡ ክቡር | Album = Kebur Kebur | Track = 3 | Year = | Lyrics =

 
ትውስ ፡ ሲለኝ ፡ የጌታዬን ፡ ፍቅር
ያደረገልኝ ፡ በጐልጐታ
ከአገር ፡ ወደ ፡ አገር ፡ በመንከራተት
ፀሐይና ፡ ውርጭ ፡ ሲፋረቁበት

ይሁዳ ፡ ሸጦት ፡ ጴጥሮስ ፡ ሲክደው
ተከታዮቹም ፡ ጥለውት ፡ ሲሸሹ
የፊጥኝ ፡ ታስሮ ፡ ለፍርድ ፡ ሲነዳ
ጥፊ ፡ እና ፡ ግርፉ ፡ ሲወርድበት

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ

አልራሩለትም ፡ አስረው ፡ ሲገርፉት
ያን ፡ መልከመልካም ፡ እሩፍሩሁን ፡ ፈጠሪ
የማይችለውን ፡ መስቀል ፡ አሲዘው
መድህናቸውን ፡ ለፍርድ ፡ ሲወስዱ

ሲጮህ ፡ ሲያነባ ፡ በጣር ፡ ተከቦ
በደም ፡ ላብ ፡ ባሕር ፡ ሆኖ ፡ ሲያነባ ፡ ሲያነባ
ሲወድቅ ፡ ሲነሳ ፡ አባ ፡ አባ ፡ ሲል
ተሰቃየልኝ ፡ ነፍሱ ፡ እስክትዘልቅ

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ

ይረሳኛል ፡ ወይ ፡ ያ ፡ የጣር ፡ ጊዜው
መድሃኒቴን ፡ እየተሳለቁበት
ከመስቀል ፡ ውረድ ፡ ራሽን ፡ አድን
እያሉ ፡ ጠላቶች ፡ ሲያሾፉበት

ጨለማ ፡ ውጦን ፡ የነበርነውን
እኛን ፡ ለማዳን ፡ ከክብሩ ፡ ወርዶ
የዓለምን ፡ ኀጢአት ፡ ያስወገደውን
ታላቁን ፡ መድህን ፡ ነፍሴ ፡ አትረሳውም

አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ (፪x)