Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Tedegefiewalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው
አልበም ሥራዬን የሠራህልኝ


አሃሃ ለሚመኩበት አሃሃ ጋሻ ይሆናል
አሃሃ ተስፋ ላደረጉት አሃሃ መች ያሳፍራል (፪x)


መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ
ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ
ምን ይሆን ብዬ (፪x)


ደመናን አይቼ ይዘንባል አልልም
ጐተራዬ ሞልቷል ብዬ አልደገፍም (፪x)


መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ
ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ
ምን ይሆን ብዬ (፪x)


ተደግፌዋለሁ አሃሃ ታምኜበታለሁ ኦሆሆ (፬x)
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)


አይሸነጋጋልም እውነት ይናገራል
ያለውን ሊፈጽም በቃሉ ይተጋል (፪x)


መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ
ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ
ምን ይሆን ብዬ (፪x)


አሃሃ ሃሰትን አያውቅ አሃሃ ቃሉ እውነተኛ
አሃሃ ያለውን ሊያደረግ አሃሃ ታማኝ ነው ጌታ (፪x)
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)


ተደግፌዋለሁ አሃሃ ታምኜበታለሁ ኦሆሆ (፬x)
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)


አልፋና ኦሜጋ ጌታ ኤልሻዳይ ነው
ዛሬም ሊሚጠሩት እርሱ ሁሉን ቻይ ነው (፪x)


የሚያኮራ ነው የሚያስተማምን
ጌታን የያዘ ከቶ ምን ሊሆን እስኪ ምን ሊሆን (፪x)


አሃሃ ዘለዓለም ነዋሪ
አሃሃ እርጅና አያውቀው
አሃሃ አልፋና ኦሜጋ
አሃሃ እርሱ ብቻ ነው (፪x)


ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)