Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Sew Ayresam

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው
ርዕስ ሰው አይረሳም
አልበም ሥራዬን የሠራህልኝ


አዝ
ሰው አይረሳም ጌታ
ሰው አይረሳም ኢየሱስ (፪x)


እንደ ሰው አይደለም ጌታ
እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (፪x)


ፍቅሩ አይቀዘቅዝ ወረት አያውቀው
እንደ ጌታ ያለ የትም አይገኝም
የተናገረውን ቃሉ ይፈጽማል
ተናግሮ ማድረግ እርሱ ብቻ ያውቃል

አዝ
ሰው አይረሳም ጌታ
ሰው አይረሳም ኢየሱስ (፪x)


እንደ ሰው አይደለም ጌታ
እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (፪x)


ማክበርና ማንሳት ጌታ ያውቅበታል
እርሱን የተጠጋ የቱ መሽቶበታል
እንደ ንጋት ብርሃን ክብሩ እየጨመረ
አቀማጥሎ ያኖራል እንዲህ እያከበረ


አዝ
ሰው አይረሳም ጌታ
ሰው አይረሳም ኢየሱስ (፪x)


እንደ ሰው አይደለም ጌታ
እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (፪x)


የቱነው የተረሳ ማነው የሚጸጸት
ሳይታሰብ ኖሮ ጊዜው ያለፈበት
የተጣለው ይልቅ ከፍ ከፍ አድርጐ
ደስታ ይሰጠዋል እንባን ከዓይኑ ጠርጐ


አዝ
ሰው አይረሳም ጌታ
ሰው አይረሳም ኢየሱስ (፪x)


እንደ ሰው አይደለም ጌታ
እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (፪x)


አይጠረጠርም ይታመናል እንጂ
እንኳን ቤቱ ኖሮ አድጐ በእርሱ እጂ
ያሳልፍለታል ዘመኑን በተድላ
እርዳኝ ብሎ መጥቶ የቱ ሰው ተጐዳ


አዝ
ሰው አይረሳም ጌታ
ሰው አይረሳም ኢየሱስ (፪x)


እንደ ሰው አይደለም ጌታ
እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (፪x)