Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Laychelemebegn

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ላይጨልምብኝ ፡ አንዴ ፡ አብርቶት ፡ ጌታ ፡ ነገሩን ፡ ሁሉ ፡ ገልብጦ (፪x)

ያለፈውን ፡ እንዳላስበው ፡ እንቅፋቶቹን ፡ አነሳሳቸው (፪x)

ጨለማዬን ፡ አበራኸው ፡ እንደፈሳሽ ፡ አሳለፍከው : ጐህ ፡ ቀደደ ፡ ቀን ፡ ሊወጣ ፡ ማረፊያዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ :

መኖሪያዬ ፡ አንተ ፡ ሆንክልኝ ፡ ከጭንቀቴ ፡ አሳለፍከኝ/ገላገልከኝ (፪x)

ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x)

እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው :

እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ

ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን

ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ

ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x)


ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x)

ከፊት ፡ ከፊቴ ፡ ጌታዬ ፡ ወጣና እሾሁን ፡ ሁሉ ፡ አነሳሳና (፪x) አደላደለው ፡ ሕይወቴ ፡ ቀና ይመራኝ ፡ ጀመር ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)

እረዳቴ ፡ ሆነህልኝ ፡ ተሸክመህ ፡ አሻገርከኝ አልነደፈኝ ፡ እባብ ፡ ጊንጡ : መች ፡ አገኘን ፡ እንደ ፡ ምኞቱ

ከፍ ፡ ላድርግህ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ ደስ ፡ ያሰኝህ ፡ ምሥጋናዬ (፪x)

ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x)

እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x)

ያ ፡ ደመና ፡ እንዳያልፍ ፡ የለም ፡ ሲያስገመግም: ጠላቴም ፡ ሲለኝ ፡ የሚያድንህ ፡ የለም : ኧረዳቴ ፡ ግን ፡ እጁን ፡ ዘረጋ ፡ ከሰማያት እኔን ፡ ሊያወጣ ፡ ፈጥኖ ፡ ከሞት

አንተ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጌታ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ
ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ

ምን ፡ ልበልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምን ፡ ልበልህ ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምን ፡ ልክፈልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልክፈል