Yosef Kassa/Zemetaw/Yihie New Yegebagn

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ ካሳ ሌላ ሥም ጆሲ ርዕስ ይሄ ነው የገባኝ አልበም ዝምታው

ውሰድልኝ ዛሬ ከነፍሴ የሆነ አምልኮዬን

አላገናኘውም ከሁኔታ ጋራ ዝማርዬን

ተላንት አመስግኜ ዛሬን አላማህም እንዲህ ብዬ

ይጨምራል እንጂ አላሳንሰውም ምስጋናዬ


የማየው ነገር ከምስጋናዬ አያግደኝም

የምሰማው አንተን ከማምለክ አያስቆመኝም

ምድረበዳዬን አለምልሞታል እያየ አይኔ

በህሩን ከፍሎ ያሻግረኛል አምናለሁ እኔ


አዝ ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር

ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪x)

የለመንኩትን የጠየኩትን ጥያቄ ሁሉ

ከምስጋና ጋር እጠብቃለሁ አምኜ ቃሉን

የከበደኝን ሸክሜን ሁሉ በእርሱ ላይ ጥዬ

በአንዳች ነገር አልጨነቅም አለ ጌታዬ


አዝ ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪x)


ደመና የለም አይታየኝም በዓይኔ

ነፋሥም የለም አይታየኝም በዓይኔ

ሳላይ አምናለሁ እንዲሀ ይሆናል

ባዶ ሸልቆ ውኃ ይሞላል


አዝ ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪x)

ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ አይቻለሁኝ ሲሰራ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ ክንደ ብርቱ ነው ኃይለኛ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ ድንቅ ነው ተአምረኛ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ አይቻለሁኝ በዓይኔ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ