ተነሺና ፡ አብሪ (Teneshina Abri) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

Yosef Kassa 2.jpg


(2)

ተነሺና ፡ አብሪ
(Teneshina Abri)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ብርሃንሽ ፡ ወጥቷልና ፡ ኢትዮጵያ

አዝ፦ ተነሺና ፡ አብሪ (፰x)

የሃያላን ፡ የታላቅ ፡ ሀገር ፡ ታሪክሽ
የተስፋ ፡ ቃል ፡ የወንጌልም ፡ ዘር ፡ ያለብሽ
ሰላምሽ ፡ ርቆ ፡ ብዙ ፡ ደም ፡ ፈሶብሻል
የስልጣኔ ፡ መጨረሻ ፡ ተብለሻል
የመከራ ፡ ሌሊትሽ ፡ ነጋ ፡ በርሱ ፡ ጊዜ
የምታበሪበት ፡ ዘመን ፡ ነው ፡ የሕዳሴ

ኢትዮዽያ ፡ ኢትዮዽያ
የከፍታ ፡ ዘመንሽ ፡ ሆነልሽ (፪x)

አዝ፦ ተነሺና ፡ አብሪ (፰x)

ብሎም ፡ ለአፍሪካ ፡ ደሞም ፡ ለአውሮፓ ፡ ለዓለም ፡ ሕዝቦች ሁሉ
ብርሃንሽ ፡ ወጣ ፡ ትንሳኤሽ ፡ መጣ ፡ ክብርሽን ፡ አዩ
የፈጣሪሽ ፡ ፊት ፡ ወዳንቺ ፡ ዞረ ፡ ልብሽ ፡ ተመልሶ
ሁሉም ፡ እንዲያይሽ ፡ እንድታበሪ ፡ እጅሽን ፡ ይዞ

አዝ፦ ተነሺና ፡ አብሪ (፰x)

የፖለቲካ ፡ የኢኮኖሚ ፡ ቀውስ ፡ ሁሉ
ከሠማይ ፡ ትእዛዝ ፡ ሲወጣ ፡ ሰላም ፡ ሆኑ
ዘረኝነትና ፡ ጥላቻ ፡ ቦታ ፡ አጣ
የፍቅር ፡ መንፈስ ፡ ሕዝቡን ፡ ሁሉ ፡ ይዞ ፡ መጣ
የዘንዶውን ፡ ራስ ፡ አምላክሽ ፡ ቀጥቅጦታል
አዝመራሽ ፡ ሁሉ ፡ ተባርኳል ፡ ፈውሶሻል

ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ
የከፍታ ፡ ዘመንሽ ፡ ሆነልሽ (፪x)

አዝ፦ ተነሺና ፡ አብሪ (፰x)

ብሎም ፡ ለአፍሪካ ፡ ደሞም ፡ ለአውሮፓ ፡ ለአለም ፡ ሕዝቦች ፡ ሁሉ
ብርሃንሽ ፡ ወጣ ፡ ትንሳኤሽ ፡ መጣ ፡ ክብርሽን ፡ አዩ
የፈጣሪሽ ፡ ፊት ፡ ወዳንቺ ፡ ዞረ ፡ ልብሽ ፡ ተመልሶ
ሁሉም ፡ እንዲያይሽ ፡ እንድታበሪ ፡ እጅሽን ፡ ይዞ

አዝ፦ ተነሺና ፡ አብሪ (፰x)

በረሃብ ፡ በስደት ፡ ሕዝብሽ ፡ ተበትኖ
ሲናቅ ፡ ሰው ፡ ሃገር ፡ የሰቀቀን ፡ ኑሮ
የናቁሽ ፡ ሁሉ ፡ የተጠየፉሽ
ጊዜው ፡ ሲመጣ ፡ ይኸው ፡ ሠገዱልሽ

ቀና ፡ በይ ፡ ከእንግዲህ
ቀና ፡ በይ ፡ ጊዜሽ ፡ ነው
ቀና ፡ በይ ፡ አትፍሪ
ቀና ፡ በይ ፡ አብሪ