ያሻግራል ፡ ማዶ (Yashageral Mado) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ከቁጥር ፡ አለፈ ፡ በዛ (፪x) ፡ ምህረቱ
ተዐምራቱን ፡ አየሁ ፡ በዐይኔ (፪x) ፡ በየዕለቱ
አምላኬ ፡ አቤቱ (፬x) ፡ ብዙ ፡ ተዐምራቱ

ሚሳሳልኝ ፡ የሚወደኝ ፡ ነፍሴም ፡ የምትወደው
የልቤ ፡ አምላክ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው
ምህረቱ ፡ ቸርነቱ ፡ ይከታተሉኛል
የእግዚአብሔርን ፡ ብርቱ ፡ ፍቅር ፡ እንዳይ ፡ ያደርጉኛል ፡ አዎ
ሆሆ ፡ እባርከዋለሁ (፪x) ፡ ነፍሴን ፡ አፈስለታለሁ ፡ አዎ

አዝ፦ ከቁጥር ፡ አለፈ ፡ በዛ (፪x) ፡ ምህረቱ
ተዐምራቱን ፡ አየሁ ፡ በዐይኔ (፪x) ፡ በየዕለቱ
አምላኬ ፡ አቤቱ (፬x) ፡ ብዙ ፡ ተዐምራቱ

ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ ፡ ጊዜ ፡ የማይለውጠው
ሁኔታዎች ፡ ማያግዱት ፡ እኔስ ፡ እርሱን ፡ አየሁ
ሺ ፡ አንደበት ፡ አይገልጸውም ፡ የእርሱን ፡ ውለታ
ብሰዋለት ፡ ምሥጋናዬን ፡ ዛሬም ፡ በደስታ
ሆሆ ፡ እባርከዋለሁ (፪x) ፡ ነፍሴን ፡ አፈስለታለሁ ፡ አሃ

ምሥጋና (፫x) ፡ ምሥጋናዬ
ለባለውለታዬ ፡ አሃሃሃ ፡ ታብሶልኛል ፡ እምባዬ ፡ አሃሃሃ
ለባለውለታዬ ፡ አሃሃሃ ፡ ተከፍሎልኛል ፡ ዕዳዬ ፡ አሃሃሃ

አዝ፦ ያሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ውዴ ፡ ያሻግራል
ታሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ሁሉን ፡ ያሻግራል
ተሻገርኩት ፡ እኔስ ፡ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ፡ ክንዶቹን ፡ እንደገና
አምላኬ ፡ ገናና (፭x)

ታላቁን ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ በድንቅ ፡ የከፈለ
ህዝቡን ፡ በተዐምር ፡ በድል ፡ ያሻገረ
ያ ፡ የቀድሞው ፡ ክንዱ ፡ መቼ ፡ ደከመና
አየሁኝ ፡ ሲያሻግር ፡ ህዝቡን ፡ በምሥጋና (፪x)

አዝ፦ ያሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ውዴ ፡ ያሻግራል
ታሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ሁሉን ፡ ያሻግራል
ተሻገርኩት ፡ እኔስ ፡ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ፡ ክንዶቹን ፡ እንደገና
አምላኬ ፡ ገናና (፭x)

አስፈሪውን ፡ ማዕበል ፡ በስልጣን ፡አዘዘው
የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ ጸጥ ፡ አደረገው
እኔም ፡ አመለጥኩኝ ፡ በክንዶቹ ፡ ብርታት
ልውደቅ ፡ በእግሮቹ ፡ ስር ፡ እጥፍ ፡ ልስገድለት
አሃ ፡ ይህም ፡ አነሰበት

አዝ፦ ያሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ውዴ ፡ ያሻግራል
ታሻግራል ፡ ማዶ ፡ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ፡ ሁሉን ፡ ያሻግራል
ተሻገርኩት ፡ እኔስ ፡ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ፡ ክንዶቹን ፡ እንደገና
አምላኬ ፡ ገናና (፭x)

Navigation menu