Yosef Bekele/Mahetemien Yefetah/Mahetemien Yefetah

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ክበር ክበር (፪x) ንገሥ ንገሥ (፪x) ክበር ክበር (፪x) ንገሥ ንገሥ (፪x) ክበር እልሃለሁ ጌታ አንተ የእኔ አለኝታ ንገሥ እልሃለሁ ኢየሱስ የሕይወቴ ንጉሥ

አዝ፦ ማኅተሜን የፈታህ ቀንበሬን ሰበርከው የዕዳ ጽፈቴን በአንዴ ደመሰስከው ጨለማዬ በርቷል ነጻ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x)

ክፉዬን የማትወደው ሁሌ የምትሳሳልኝ ስለእኔ የምትማልድ አባቴ እኮ አለኸኝ በቀራኖዮ ታሪክን ሰርተህ ጠላቴን አሸንፈሃል ያሰረኝ ትብታብ ተፈቶ ዛሬማ ያዘምረኛል (፪x) ዛሬ እንዲህ ያዘምረኛል

ዛሬም ሃሌሉያ ነገም ሃሌሉያ ሁሌም ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (፫x)

አዝ፦ ማኅተሜን የፈታህ ቀንበሬን ሰበርከው የዕዳ ጽፈቴን በአንዴ ደመሰስከው ጨለማዬ በርቷል ነጻ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x)

ጨለማ በአንተ ዘንድ የለም ብርሃን ነህ ሁሌ ምትበራ የንጋቱ ኮከብ ኢየሱስ ብርሃን ለጨለማ አንተ ስትመራኝ ረድኤቴ አረማመዴ ቀናልኝ ብሩህ ተስፋን አይቻለሁ ኢየሱስ ከፍ በልልኝ ኢየሱስ ከፍ በልልኝ አባቴ ከፍ በልልኝ

ዛሬም ሃሌሉያ ነገም ሃሌሉያ ሁሌም ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (፫x)

አዝ፦ ማኅተሜን የፈታህ ቀንበሬን ሰበርከው የዕዳ ጽፈቴን በአንዴ ደመሰስከው ጨለማዬ በርቷል ነጻ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x)

ፍቅርህ ከአይምሮ በላይ ነው ምህረትህ እጅግ የበዛ ጥሩ ነህ ለእኔስ ኢየሱስ ሆንክላት ለነፍሴ ቤዛ ብቻህን ተዐምራት ሰርተህ መንጥቀህ አውጥተኸኛል እርግማኔን አነሳኸው በረከትህ አግኝቶኛል በረከትህ አግኝቶኛል (፪x)

ክበር ክበር (፪x) ንገሥ ንገሥ (፪x) ክበር ክበር (፪x) ንገሥ ንገሥ (፪x) ክበር እልሃለሁ ጌታ አንተ የእኔ አለኝታ (አ ኢየሱስ) ንገሥ እልሃለሁ ኢየሱስ የሕይወቴ ንጉሥ

አዝ፦ ማኅተሜን የፈታህ ቀንበሬን ሰበርከው የዕዳ ጽፈቴን በአንዴ ደመሰስከው ጨለማዬ በርቷል ነጻ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፰x)