ማደሪያህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (Maderiyah Denq New) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

 
አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው
ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው
ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ
(፪x)
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ
ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x)

አእላፋት ፡ መላእክት ፡ በፊትህ
ቅድስናህን ፡ ሚያውጁልህ
ዙፋንህ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ገናና
በምሥጋናም ፡ የተፈራህ
ድምጽህ ፡ እንደብዙዎች ፡ ነው
ቃልህ ፡ ከማር ፡ እልቅ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው
በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ዙፋኑ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ የልቤ
በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ዛሬም ፡ ሾሜሃለሁ ፡ በላዬ

አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው
ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው
ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ
(፪x)
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ
ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x)

አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ
እኔስ ፡ አላየሁም ፡ እንደአንተ
ፍጥረት ፡ ተደነቀ ፡ በስራህ
አቤት ፡ የእኔስ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ
በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ገብተሃል
ማደሪያ ፡ ቤትህ ፡ አድርገሃል
አኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላምልክህ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ
እኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላክብርህ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ

ኢየሱሴ ፡ ጌታዬ ፡ አምባዬ ፡ ጋሻዬ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ እንደአንተ ፡ ማነው
በጨለማው ፡ ሌሊት ፡ ፈጥኖ ፡ ሚደርሰው
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ባርኮ ፡ አጸለችም
ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

አምላኬ ፡ አሃ ፡ ያደረከው ፡ ነገር ፡ ለእኔ
የሰራኸው ፡ ስራ ፡ በዘመኔ
ቢነገር ፡ ቢነገር ፡ ስጦታህ
መች ፡ ያልቃል ፡ ጌታዪ ፡ ደግነትህ
መች ፡ ያልቃል ፡ አባትዬ ፡ ደግነትህ
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ስጦታህን
መች ፡ ያልቃል ፡ ኢየሱስዬ ፡ በጐነትህ
መች ፡ ያልቃል ፡ ወዳጄ ፡ በጐነትህ


Navigation menu